የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ማስ/ጽ/ቤት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት እና ከጋሞ ዞን ጋር በመተባበር የግድቡ ግንባታ የተጀመረበት 13ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ «የአባይ ዘመን ትውልድ ታላቅ የሥነ ጽሑፍ  ምሽት» “በኅብረት ችለናል!” በሚል መሪ ቃል ግንቦት 09/2016 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው ያካሂዳል፡፡ በዕለቱ መርሃ ግብር ላይ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ላይ ያተኮሩ ግጥሞችንና አጭር ትውን ተውኔቶችን ማቅረብ የምትችሉ ተማሪዎች የሥነ ጽሑፍ ሥራዎቻችሁን ዩኒቨርሲቲው አወዳድሮ ከ1ኛ - 3ኛ የወጡ የተማሪዎች የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች በመድረኩ እንዲቀርቡ ዕድል ለመስጠት ስለተፈለገ ከሚያዝያ 15-30/2016 ዓ/ም ድረስ ሥራዎቻችሁን በዩኒቨርሲቲው ኢ-ሜይል አድራሻ፡- This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ወይም This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. በመላክ ወይም የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት የመወዳደሪያ ጽሑፋችሁን በሶፍት ኮፒ በመያዝ  በአካል በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጸ ተማሪዎቻችን ዕድሉን በማግኘትና በዚህ ሀገራዊ መድረክ ላይ በመገኘት በሥነ ጽሑፍ ጥበብ የበኩላችሁን መልዕክት እንዲታስተላልፉ ከወዲሁ ያሳውቃል፡፡

 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት