የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ለዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት ከዩኒቨርሲቲው መምህራን መካከል አወዳድሮ ለመመደብ ይፈልጋል፡፡

የአመልካቾች ትምህርት ደረጃ ሁለተኛ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከማመልከቻቸው ጋር ቀጥሎ የተዘረዘሩ ማስረጃዎችን በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. Curriculum vitae (CV)
  2. የትምህርት ደረጃን የሚገልጽ ሰርተፊኬት አንድ ፎቶ ኮፒ፤
  3. የአካዳሚክ ማዕረግ የሚገልጽ ደብዳቤ፤
  4. በዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ወይም በምርምር ተቋም በተመራማሪነት ያገለገሉበትን ጊዜ የሚገልጽ ደብዳቤ፤
  5. በዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉበትን የሚገልጽ ደብዳቤ፤
  6. በዩኒቨርሲቲው በአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንትነት ቢመደቡ የዘርፉን ሥራ ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂክ ዕቅድ በዝርዝር ማቅረብ የሚችል/ትችል፡፡

ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ከመስከረም 18-29/2013 ዓ.ም በሥራ ሰዓት ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ቦርዱ ይገልጻል፡፡

የአርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ