ለአርባ ምንጭ ዩነቨርሲቲ የ2012 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ተግባቦት አማራጮች ተመራቂ ተማሪዎች ጥቅምት 25 እና 26 ግቢ እንድትገቡ ከጥቅምት 03/2013 ዓ/ም ጀምሮ ያስተዋወቀ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በተፈጠረው አሁናዊ አገራዊ ሁኔታ ምክንያት ከተለያዩ አከባቢዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር የተፈጠረ መሆኑን መገንዘብ ችለናል፡፡


ስለሆነም ውድ ተመራቂዎቻችን ከሁሉም በላይ ደኅንነታችሁ የሚበልጥ መሆኑን በመገንዘብ ሁኔታዎች ሲስተካከሉ በቀጣይ ጊዜ በድጋሚ ማስታወቂያ የመግቢያ ጊዜ እስከሚገለፅ ድረስ በያላችሁበት እንድትቆዩ እንዲሁም ይህንን ማስታወቂያ ሳያነቡ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን ለሚደርሱ ተማሪዎችም ሁሉም ተመራቂዎች ሳይገቡ ትምህርት የማይጀመር መሆኑን እያሳወቅን በተፈጠረው ሁኔታ ከልብ ማዘናችንን እንገልፃለን፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት