‹‹Computing and Software Engineering›› ፋከልቲ በ‹‹Artificial Intelligence(AI)›› እና ‹‹Large Language Models(LLMs)›› ዙሪያ ለመምህራንና ለቅድመና ድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የካቲት 15/2016 ዓ/ም ሴሚናር አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የፋከልቲው ዲን መ/ር ጌታሁን ትዕግሥቱ እንደገለጹት ሰው ሠራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እንደ ሰው እንዲያስብና እንዲሠራ ተደርጎ የተሠራ ቴክኖሎጂ ሲሆን ሰው አልባ መኪኖች፣ ሮቦቶችና ድሮን የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎች በአጭር ጊዜ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያደርግ ነው፡፡ ‹‹Large Language Models (LLMs)››፣ ‹‹Chat GTP›› እና ‹‹Google bard››ን አስመልክቶ ማኅበረሰቡ የጠለቀ ግንዛቤ የለውም ያሉት ዲኑ አገልግሎታቸውን ለአካዳሚክ ማኅበረሰቡ ለማስተዋወቅ ሴሚናሩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

የፋከልቲው መምህርና የሴሚናሩ አዘጋጅ ዶ/ር መሐመድ አበበ ሰው ሠራሽ አስተውሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተቋም ተከፍቶለት እየተሠራበት መሆኑን ተናግረው ዩኒቨርሲቲው እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ቴክኖሎጂውን በተመለከተ ለተማሪዎችና ለመምህራን በማሳወቅ እንዲጠቀሙበት ማድረግ ስለሚያስፈልግ ሴሚናሩ ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡

ሌላኛው የፋከልቲው መምህርና የሴሚናሩ አዘጋጅ ዶ/ር መሳይ ሳሙኤል በበኩላቸው ‹‹Large Language Models(LLMs) ለ2 እና ለ3ዲግሪ ተማሪዎች ለምርምር ሥራ ስለሚረዳ ሴሚናሩ ስለቴክኖሎጂው ያላቸውን ዕውቀት አሳድገው በአግባቡ መጠቀም እንዲችሉ ያግዛል ብለዋል፡፡

የሴሚናሩ ተሳታፊዎች ቴክኖሎጂን የት፣ እንዴት፣ በምን መልክ መጠቀም እንዳለባቸው ጠቅለል ያለ መረጃ ማግኘታቸውን ተናግረው ሁሉም አካዳሚክ ማኅበረሰብ መረጃውን ቢያገኝ በእጅጉ ተጠቃሚ እንደሚሆን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት