ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ለተወጣጡ መምህራን በኮንስትራክሽን ሶፍትዌሮች ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ

በኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከ8 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ለተወጣጡ መምህራን solid work እና Arc cad በተሰኙ የኮንስትራክሽን ሶፍትዌሮች ዙሪያ ከሚያዝያ 1/2011 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

የቴክኖሎጂ ሽግግር ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ወንድማገኝ ጌታቸው እንደገለፁት ሠልጣኝ መምህራን በየኮሌጃቸው ለሚገኙ ተማሪዎች ያገኙትን ዕውቀት ማጋራት እንዲሁም በአካባቢያቸው የሚገኙ በተለይ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ተቋማት የሚጠቀሟቸው የአሠራር ዘዴዎች በቴክኖሎጂ የተደገፉ እንዲሆኑ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የሜካኒካልና ፕሮዳክሽን ምህንድስና ፋካልቲ መምህርና አሠልጣኝ አዳነ ካሳ በበኩላቸው ሠልጣኞች በሶፍትዌሮቹ አጠቃቀም ዙሪያ ያገኙትን መሠረታዊ ዕውቀት በራሳቸው በማዳበር ለተማሪዎቻቸው ማስተላለፍ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

የጂንካ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ መምህር አቶ ዳንኤል ደሳለኝ እንደተናገሩት ከቴክኖሎጂ ጋር መቀራረባችን የክህሎት ክፍተታችንን ለመቅረፍ ጉልህ ሚና ስለሚኖረው መሰል ሥልጠናዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል፡፡

ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት