የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኅብረት የ2013 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የፓርላማ ስብሰባውን ‹‹ሰላማዊና ምቹ የመማር ማስተማሪ ሂደት እንዲኖር ኅብረታችን ትልቁን ሚና ይጫወታል›› በሚል መሪ ቃል መጋቢት 19/2013 ዓ.ም አካሂዷል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና የጋሞ ዞን አስተዳደር በምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የትብብር መግባቢያ ስምምነት መጋቢት 21/2013 ዓ/ም ተፈራርመዋል፡፡

በመግባቢያ ስምምነቱ ዞኑና ዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰቡን ሕይወት በዘላቂነት መቀየር በሚያስችሉ የምርምር፣ የማኅበረሰብ አገልግሎት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የአቅም ግንባታ ዘርፎች ላይ በጋራ እንደሚሠሩ ተቀምጧል፡፡ ስምምነቱ ለ4 ዓመታት የሚቆይ ሲሆን ሁለቱ አካላት የሰው ሀብት፣ ቁሳቁስና ፋይናንስ በጋራ እንደሚጠቀሙ በስምምነቱ ተጠቅሷል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴርና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዘጋጅነት 9ኛው ‹‹የሕክምና ት/ቤቶች ካውንስል በኢትዮጵያ›› ጉባዔ ከመጋቢት 16-17/2013 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ፓራዳይዝ ሎጅ አካሂዷል፡፡   ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂዎች፣ ፕሮግራሞች፣ የዘርፉ የ10 ዓመት የልማት ፍኖተ ካርታና ሌሎች ተያያዥ ሰነዶች ዙሪያ እየተሰጠ የሚገኘው ሥልጠናዊ ውይይት በዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች እየተካሄደ ነው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ110ኛ በሀገራችን ለ45ኛ ጊዜ የተከበረው ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ‹‹የሴቶችን መብት የሚያከብር ማኅበረሰብ እንገንባ›› በሚል መሪ ቃል መጋቢት 8/2013 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው ተከብሯል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ በመክፈቻ ንግግራቸው ሴቶች የኅብረተሰቡ ግማሽ አካል በመሆናቸው በአንድ ሀገር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ጉልህ ሚና ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል፡፡ በተለያዩ ተፅዕኖዎች ምክንያት የሴቶች ተሳትፎ ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር ያነሰ ነው ያሉት ፕሬዝደንቱ አሁን በደረስንበት የዕድገት ደረጃ በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገራችን በሁሉም መስኮች የሴቶች ተሳትፎ በመጠንና በውጤታማነት ትልቅ ዕድገት እያሳየ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲውን ለሴት ተማሪዎች ምቹ ለማድረግ ሁሉም በትብብር መሥራት እንደሚጠበቅበትም ፕሬዝደንቱ አሳስበዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ