Arba Minch University in association with Ethiopian Public Health Institute (EPHI) has organized a 2-day workshop on multi-sectoral inter-disciplinary research findings on moringa stenopetala at New Hall, Main Campus, from 26th to 27th February, 2021. The 1st day saw presentation of 9 research findings that generated a much-needed synergy where researchers, academicians, officials and different stakeholders could discuss the multiple medicinal, epidemiological, biochemical and health benefits of moringa for the society. Click here to see the pictures

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቤኔፊት ሪያላይዝ (BENEFIT-REALISE) ፕሮግራም የ2 ዓመታት ዞናዊ አፈፃፀሙ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የካቲት 16/2013 ዓ/ም ወርክሾፕ አዘጋጅቷል፡፡ ፕሮግራሙ ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜያት የቀሩት በመሆኑ መልካም ተሞክሮዎችን በዘላቂነት ለማስፋፋት ከባለድርሻ አካላቱ የሚጠበቁ ሥራዎችና ኃላፊነቶች በመድረኩ በሰፊው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በሥሩ 6 ፕሮጀክቶችን ይዞ ላለፉት 5 ዓመታት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና አካባቢው ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን ሲሠራ የቆየው IUC ፕሮግራም በገለልተኛ አካላት በተደረገ የአፈፃፀም ግምገማ የላቀ ውጤት በማስመዝገቡ የ2ኛ ዙር የ5 ዓመት ዕድል ማግኘቱ ተገልጿል፡፡

የፕሮግራሙ ኃላፊ ዶ/ር ፋሲል እሸቱ እንደገለጹት IUC ፕሮግራም በሁለት ዙር የተከፈለ የ10 ዓመት ቆይታ ያለው ሲሆን 2ኛው ዙር ዕድል የሚወሰነው በመጀመሪያው ዙር በሚመዘገበው ውጤት ነው፡፡ በዚህም መሠረት ላለፉት ዓመታት የተማሪዎችን ውጤታማነት፣ የፋይናንስና የአፈፃፀም ሪፖርቶችንና ሌሎችም ሥራዎችን በለጋሽ አካሉ ተመርጦ የመጣው ገለልተኛ ገምጋሚ ቡድን በአካል በመገኘት ባደረገው የአፈፃፀም ግምገማ ፕሮግራሙ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ በመቻሉ 2ኛ ዙር ዕድል ማግኘት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የምርምር ዳይሬክቶሬት ከቴክኖሎጂና ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች ለተወጣጡ መምህራንና ተመራማሪዎች በምርምር አጻጻፍ ሳይንሳዊ ስነ-ዘዴ ዙሪያ ከየካቲት 9-11/2013 ዓ.ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ የምርምር ንድፈ ሃሳብ አሰባሰብና አጻጻፍ፣ የምርምር ግኝቶች አዘገጃጀትና አጻጻፍ እንዲሁም በታወቁ ጆርናሎች ላይ የሚወጡ ምርምሮች አጻጻፍ ስነ-ዘዴ የሥልጠናው ትኩረቶች ናቸው፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ነፃ፣ ገለልተኛና ብቃት ያለው የአገልግሎት ዘርፍን በተቋማት ውስጥ ለማጠናከር የሚረዳ የአሠልጣኞች ሥልጠና በሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር እና በተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ጥር 27/2013 ዓ.ም ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ተሰጥቷል፡፡

ነፃ፣ ገለልተኛና ብቃት ያለው የአገልግሎት ዘርፍ ግንባታ፣ የሰው ሀብት ልማትና ብቃት ማረጋገጫ ሥርዓት፣ የመንግሥት አገልግሎት እሴት ግንባታ እንዲሁም ሥነ-ምግባርና ጥራት ያለው የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ሥልጠናው በዋናነት ትኩረት ያደረገባቸው ነጥቦች ናቸው፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ