• የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ በዓል

 • የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 87 የሕክምና ዶክተሮችን በመጪው ቅዳሜ ያስመርቃል

 • 33rd virtual graduation ceremony for Master and Undergraduate students on 5th Sept.

 • አርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ለ33ኛ ጊዜ ሊያስመርቅ ነው

 • Welcome to Arbaminch University

 • ዩኒቨርሲቲው 140 የሕክምና ዶክተሮችን ሊያስመርቅ ነው

 • 6th batch Medical Doctors graduation

 • ICT In education-university school partnership project

 • አንድ ቅዳሜን ለህዝቤ

 • አቶ ኦባንግ ሜቶ በዩኒቨርሲቲያችን ተገኝተው ለተማሪዎቻችን በአገራዊ አንድነት፣ የሠላምና የመቻቻል እሴት ግንባታ ዙሪያ የማነቃቂያ ንግግር ያደርጋሉ

 • 5th batch of Doctors of Medicine to be graduated on 1st December

 • Happy New Year, 2011 E.C

 • Welcome to Arba Minch University!

ለውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የሶፍትዌሮች ሥልጠና ተሰጠ

Friday, 27 November 2020 17:15

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን ማኅበር፣ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት በመተባበር ለውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የውሃ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም በሚያስችሉ አዳዲስ ሶፍትዌሮች ዙሪያ ከጥቅምት 30 - ኅዳር 04/2013 ዓ/ም የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Read more: ለውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የሶፍትዌሮች ሥልጠና ተሰጠ

 

አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንትነት ውድድር በድጋሚ የወጣ የውስጥ ማስታወቂያ

Friday, 20 November 2020 16:24

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ የዩኒቨርሲቲውን አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት ከዩኒቨርሲቲው መምህራን መካከል አወዳድሮ ለመመደብ ይፈልጋል፡፡ አመልካቾች የትምህርት ደረጃቸው 2ኛ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከማመልከቻቸው ጋር ቀጥሎ የተዘረዘሩ ማስረጃዎችን በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

Read more: አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንትነት ውድድር በድጋሚ የወጣ የውስጥ ማስታወቂያ

ምርምርና ማኅ/አገልግሎት ምክትል ፕሬዝደንትነት ውድድር የወጣ የውስጥ ማስታወቂያ

Friday, 20 November 2020 16:19

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ የዩኒቨርሲቲውን ምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝደንት ከዩኒቨርሲቲው መምህራን መካከል አወዳድሮ ለመመደብ ይፈልጋል፡፡ አመልካቾች የትምህርት ደረጃቸው 2ኛ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከማመልከቻቸው ጋር ቀጥሎ የተዘረዘሩ ማስረጃዎችን በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

Read more: ምርምርና ማኅ/አገልግሎት ምክትል ፕሬዝደንትነት ውድድር የወጣ የውስጥ ማስታወቂያ

 

የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ት/ቤት የምርምር ንድፈ ሃሳብ ግምገማ አካሄደ

Saturday, 21 November 2020 10:08

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ት/ቤት የምርምርና ማኅበረሰብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ት/ቤት ጋር በመተባበር ከሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ፣ ከጤና ሳይንስ እና ከማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጆች የተወጣጡ መምህራን ባቀረቡት የምርምር ንደፈ ሃሳብ ላይ ኅዳር 04/2013 ዓ/ም ግምገማ አካሂዷል፡፡

የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ት/ቤት የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪ ዶ/ር ቤታ ጻማቶ እንደገለጹት የማኅበረሰቡን ችግር በሳይንሳዊ መንገድ መፍታት የሚችሉ የምርምር ንድፈ ሃሳቦችን ገምግሞ ለማሳለፍ መድረኩ ተዘጋጅቷል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Read more: የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ት/ቤት የምርምር ንድፈ ሃሳብ ግምገማ አካሄደ

‹‹በደቡብ ኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ በዓባያና ጫሞ ተፋሰስ የመሬት መራቆትን መቀነስ ለዘላቂ የመሬት አጠቃቀም›› በሚል መሪ ቃል ዓውደ ጥናት ተካሄደ

Saturday, 21 November 2020 10:03

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ IUC ፕሮጀክት ‹‹በደቡብ ኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ በዓባያና ጫሞ ተፋሰስ የመሬት መራቆትን መቀነስ ለዘላቂ የመሬት አጠቃቀም›› በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 20/ 2013 ዓ/ም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ዓውደ ጥናት አካሂዷል፡፡

ከቤልጂየም ሀገር ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ለሚደረገው ምርምር የፕሮጀክት 4 አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ደረጀ ፀጋዬ እንደገለጹት ፕሮግራሙ በዓባያና ጫሞ ሐይቆች ተፋሰስ ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን መሠረት አድርጎ ከሚያከናውናቸው የምርምር ፕሮጀክቶች አንዱ በሆነው የመሬት መራቆት ላይ ያተኮረ ሲሆን ዓላማውም በምርምር የተገኙ ውጤቶችን ለባለድርሻ አካላት በማሳወቅ ውይይት ማድረግ፣ በቀጣይ ተፋሰሱን የማከምና የማዳን ሥራዎች የሚሠሩበትን ሂደቶች ማመቻቸት እንዲሁም የተገኙ ግኝቶች ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እንዲሆኑ ማስቻል ነው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Read more: ‹‹በደቡብ ኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ በዓባያና ጫሞ ተፋሰስ የመሬት መራቆትን መቀነስ ለዘላቂ የመሬት አጠቃቀም›› በሚል መሪ ቃል ዓውደ ጥናት ተካሄደ

 

Page 5 of 269

«StartPrev12345678910NextEnd»