አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከኮንሶ ዞን ጉማይዴ አካባቢ በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ
Friday, 27 November 2020 16:40
በኮንሶ ዞንና አካባቢው በተከሰተው የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለሚገኙ ወገኖች ዩኒቨርሲቲው ልዩ ልዩ ኅዳር 15/2013 ዓ/ም ድጋፍ አድርጓል፡፡ በዕለቱ 156 ፍራሽ፣ 28 ካርቶን ሳሙና እና 5 እሽግ የሴቶች የንጽህና መጠበቂያዎች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ከተፈናቃዮቹ በቀረበው ጥያቄ መሠረትም የውሃ አቅርቦት እና የጤና አገልግሎት እየተሰጣቸው ነው፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲው ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከኮንሶ ዞን ጉማይዴ አካባቢ በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበሰረብ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ደም ለገሰ
Friday, 27 November 2020 10:12
የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ሕግ በማስከበር ሂደት ላይ ጉዳት ለደረሰባቸውና ደም ለሚያስፈልጋቸው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት አጋርነታቸውን ለመግለጽ ኅዳር 14/2013 ዓ.ም በሁሉም ካምፓሶች ደም የመለገስ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር ወ/ሮ ወይንሸት ገ/ፃዲቅ እንደተናገሩት የደም ልገሳው ዋና ዓላማ ለሀገር ሰላምና ደኅንነት መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የበኩላችንን አስተዋፅኦ ማበርከት ነው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
ሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ትምህርት ቤት የአዕምሮ ጤና፣ ሥነ-ልቦናና ማኅበራዊ አገልግሎትን በተመለከተ ሥልጠና ሰጠ
Friday, 27 November 2020 10:03
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ትምህርት ቤት ከተማሪዎች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ላላቸው የሥነ-ልቦና፣ ጋይዳንስና ካውንስሊግ እና የዜሮ ፕላን ባለሙያዎች፣ የተማሪዎች አገልግሎት ሠራተኞች እንዲሁም የተማሪዎች መኝታ ቤት፣ የምግብ አገልግሎት፣ የሰላም ፎረምና የደኅንነትና ጥበቃ አስተባባሪዎች የአዕምሮ ጤና፣ ሥነ ልቦናና ማኅበራዊ አገልግሎት አሰጣጥንን በተመለከተ ከኅዳር 10-11/2013 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ትምህርት ቤት የአዕምሮ ጤና፣ ሥነ-ልቦናና ማኅበራዊ አገልግሎትን በተመለከተ ሥልጠና ሰጠ
ለውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የሶፍትዌሮች ሥልጠና ተሰጠ
Friday, 27 November 2020 17:15
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን ማኅበር፣ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት በመተባበር ለውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የውሃ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም በሚያስችሉ አዳዲስ ሶፍትዌሮች ዙሪያ ከጥቅምት 30 - ኅዳር 04/2013 ዓ/ም የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ለውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የሶፍትዌሮች ሥልጠና ተሰጠ
አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንትነት ውድድር በድጋሚ የወጣ የውስጥ ማስታወቂያ
Friday, 20 November 2020 16:24
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ የዩኒቨርሲቲውን አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት ከዩኒቨርሲቲው መምህራን መካከል አወዳድሮ ለመመደብ ይፈልጋል፡፡ አመልካቾች የትምህርት ደረጃቸው 2ኛ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከማመልከቻቸው ጋር ቀጥሎ የተዘረዘሩ ማስረጃዎችን በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
Read more: አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንትነት ውድድር በድጋሚ የወጣ የውስጥ ማስታወቂያ
More Articles...
Page 10 of 275
«StartPrev12345678910NextEnd»