• አርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ ለ33ኛ ጊዜ ሊያስመርቅ ነው

 • የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ በዓል

 • የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 87 የሕክምና ዶክተሮችን በመጪው ቅዳሜ ያስመርቃል

 • 33rd virtual graduation ceremony for Master and Undergraduate students on 5th Sept.

 • አርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ለ33ኛ ጊዜ ሊያስመርቅ ነው

 • Welcome to Arbaminch University

 • ዩኒቨርሲቲው 140 የሕክምና ዶክተሮችን ሊያስመርቅ ነው

 • 6th batch Medical Doctors graduation

 • ICT In education-university school partnership project

 • አንድ ቅዳሜን ለህዝቤ

 • አቶ ኦባንግ ሜቶ በዩኒቨርሲቲያችን ተገኝተው ለተማሪዎቻችን በአገራዊ አንድነት፣ የሠላምና የመቻቻል እሴት ግንባታ ዙሪያ የማነቃቂያ ንግግር ያደርጋሉ

 • 5th batch of Doctors of Medicine to be graduated on 1st December

 • Happy New Year, 2011 E.C

 • Welcome to Arba Minch University!

AMU hosts 7th national meet on science for sustainable development

Monday, 19 April 2021 09:47

Arba Minch University’s Research Directorate has hosted 7th national meet on ‘Science for Sustainable Development’ at Main Campus beginning from 16th to 17th April, 2021. Researchers, academicians and professionals from across Ethiopia gathered to deliberate upon key issue of science and innovation that unleash holistic development in sustainably catering to the needs of people and alleviate their problems. Click here to see the pictures

Read more: AMU hosts 7th national meet on science for sustainable development

 

ከጋሞ ዞን ለተወጣጡ የቋንቋ ጥናት ባለሙያዎች የክሂሎት ማሻሻያ ሥልጠና ተሰጠ

Monday, 19 April 2021 09:44

የዩኒቨርሲቲው ማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የማኅበረሰብ አገልግሎት ከጋሞ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞን እና በዞኑ ከሚገኙ 14 ወረዳዎችና 4 ከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ 37 የቋንቋ ጥናት ባለሙያዎች እንዲሁም ለወረዳና ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ከሚያዝያ 4 - 7/2013 ዓ/ም በቋንቋ ጥናት ዘዴዎች፣ በመረጃ አሰባሰብ ሂደት፣ በስነ-ቃል እና በስነ-ጽሑፍ ጥናት ላይ ያተኮረ የክሂሎት ማሻሻያ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Read more: ከጋሞ ዞን ለተወጣጡ የቋንቋ ጥናት ባለሙያዎች የክሂሎት ማሻሻያ ሥልጠና ተሰጠ

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ ተከበረ

Monday, 19 April 2021 09:40

የዩኒቨርሲቲው ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት በዓለም ለ110ኛ በኢትዮጵያ ለ45ኛ ጊዜ የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ‹‹የሴቶችን መብት የሚያከብር ማኅበረሰብ እንገንባ›› በሚል መሪ ቃል መጋቢት 30/2013 ዓ/ም በሳውላ ካምፓስ አክብሯል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሪት ሠናይት ሳህሌ እንደገለጹት ማኅበረሰቡ በሴት ልጅ ላይ የፈጠረው የአመለካከት ችግር ሴቶች በራሳቸው እንዳይተማመኑ የሚያደርግ ነው፡፡ ይህንን የአመለካከት ችግር መቅረፍና ሴቶች በሴትነታቸው ምክንያት በትምህርታቸውና በሥራቸው የሚያጋጥሟቸውን ፆታዊ እንቅፋቶች በማስወገድ ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ሴቶች በብቃታቸው በአገሪቱ ቁልፍ ቦታዎች በኃላፊነት መምራታቸውና በተሰማሩበት መስክ የጎላ ለውጥ እያስመዘገቡ መሆኑ ለሌሎች ሴቶች መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Read more: ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ ተከበረ

 

ብራይት ፊውቸር አግሪካልቸር ፕሮጀክት የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጠ

Friday, 16 April 2021 18:31

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ብራይት ፊውቸር አግሪካልቸር ፕሮጀክት /BFA/ ‹‹የሥራ ፈጠራ ክሂሎትን ማሳደግ›› በሚል ርዕስ ከተለያዩ ክልሎች የግብርና እና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጆች ለተወጣጡ መምህራን ከመጋቢት 23/2013 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 8 ቀናት የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር ይስሃቅ ከቸሮ እንደተናገሩት ሠልጣኞች በራሳቸው ዘርፍ ሥራ እንዲፈጥሩና ለተማሪዎቻቸውም ማሳየት እንዲችሉ ክሂሎታቸውን ለማሳደግ የተዘጋጀ ሥልጠና ነው፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Read more: ብራይት ፊውቸር አግሪካልቸር ፕሮጀክት የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሥርዓተ ትምህርት የውስጥ ግምገማ አካሄደ

Friday, 16 April 2021 15:31

የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በውሃ አቅርቦትና ሳኒተሪ ምኅንድስና የ3ኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራም ለማስጀመር ሚያዝያ 2/2013 ዓ/ም የሥርዓተ ትምህርት የውስጥ ግምገማ አካሂዷል፡፡

የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ዓለማየሁ ጩፋሞ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብሎ እንደመለየቱ በ2ኛና 3ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥሉት 5 ዓመታት 5,000 የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ለማስመረቅ ያቀደ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ፕሮግራሙን መክፈቱ ለዚህ ሀገራዊ ዕቅድ መሳካት የበኩሉን አስተዋፅኦ የሚያበረክትበት ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Read more: የዩኒቨርሲቲው ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሥርዓተ ትምህርት የውስጥ ግምገማ አካሄደ

 

Page 2 of 283

«StartPrev12345678910NextEnd»