የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት በ2014 የትምህርት ዘመን በክረምት መርሐ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡

‹‹በተፈጠረው እድል ማኅበረሰባችንን እናገልግል›› በሚል መሪ ቃል ዩኒቨርሲቲው 7ኛውን የማኅበረሰብ ሳምንት ከሰኔ 06-12/2014 ዓ/ም በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብሯል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ክርስቲያን ኤይድ/Christian Aid /ከተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በካምባ ወረዳ ዲንጋሞ ቀበሌ ማይጸሌ ወንዝ ላይ አነስተኛ የኃይል ማመንጫ ለማስገንባት ሰኔ 12/2014 ዓ/ም የመሠረት ድንጋይ አስቀምጧል፡፡ ለሥራው ማስፈፀሚያ የሚሆነው ገንዘብ 1.1 ሚሊየን ብር በዩኒቨርሲቲውና 6.123 ሚሊየን ብር በክርስቲያን ኤይድ ግብረ ሠናይ ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መምህራን የተገኘ የምርምር ውጤት ላይ ተመሥርቶ ኮሌጁ ከዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት፣ ከጃኖ ዕደ ጥበብ ኢንተርፕራይዝ እና ከGIZ ጋር በመተባበር በጨንቻ ዶኮ ማሾ ቀበሌ ለሚኖሩ ሸማኔዎች የዘመናዊ ሽመና አሠራር ላይ ከግንቦት 20 - ሰኔ 04/2014 ዓ/ም ለ15 ተከታታይ ቀናት የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በሥራ ላይ ልምምድ የቆዩ የኮሌጁ መምህራንን ሪፖርት ሰኔ 04/2014 ዓ/ም ገምግሟል፡፡ በዕለቱ ከመንግሥትና ከግል ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችል የስምምነት መግባቢያ ሰነድም ተፈራርሟል፡፡