አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሰገንና ጨልኮ ወንዞች ላይ የመስኖ ውሃ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክቶች ዲዛይንና ጥናት ለማካሄድ ከደቡብ ዲዛይን፣ ግንባታና ቁጥጥር ባለሥልጣን ጋር ግንቦት 26/2014 ዓ/ም ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት የውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ የሰገን ወንዝ በኮንሶ ዞንና በቡርጂ ልዩ ወረዳ መካከል ሲሆን የጨልኮ ወንዝ ደግሞ በመሎ ኮዛ ወረዳ በቦረዳ ጋዘር የሚገኙ ናቸው፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ በሎጅስቲክ እና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ት/ክፍል መምህርና ተመራማሪ አቶ ሀቢብ ሳኖ “International Virtual Conference on Intelligent Computing in Humanity, Agriculture, Science & Technology” በሚል ርዕስ በተካሄደ ቨርቹዋል ኮንፈረንስ ላይ ቁልፍ ንግግር አቅርበዋል፡፡

ማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በ“ELT”፣ በ“Environment and Natural Resources Management” እና በ“Disaster Risk Management” ትምህርት ፕሮግራሞች በ3ኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ነገ ቅዳሜ ሰኔ/4/2014 ዓ/ም፣ የፊታችን ሰኞና ማክሰኞ ማለትም ሰኔ 6 እና 7/2014 ዓ/ም የመጨረሻ የምርምር ሥራቸውን የውጪና የሀገር ውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ት/ቤት አስተባባሪነት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን አጠናቀው ለተመረቁ መምህራን 3ኛው የእንኳን ደኅና መጣችሁ ‹‹የዶክተሮች ቀን/Doctoral Day›› መርሃ-ግብር ግንቦት 30/2014 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ስር በሚገኙ ሦስት ፋከልቲዎች የቀረቡ 7 የድኅረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ግንቦት 29/2014 ዓ/ም የውጭ የሥርዓተ ትምህርት ግምገማ ተካሂዷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ