የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግምገማዊ ስልጠና በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበር ሲሆን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲም ከመስከረም 8 እስከ መስከረም 12/2010 ዓ.ም ድረስ ይከናወናል፡፡

ስለሆነም ማንኛውም በሥራ ላይ ያላችሁ የዩኒቨርሲቲው መምህራንና የቴክኒክ ረዳቶች በተጠቀሰው ጊዜ በዋናው ግቢ ቁጥር 4 የመመገቢያ አዳራሽ፤ እንዲሁም የአስተዳደር ሠራተኞች በዋናው ግቢ ቁጥር 3 የመመገቢያ አዳራሽ፤ እና በጫሞ ካምፓስ የመመገቢያ አዳራሽ እንድትገኙ እያሳሰብን ሁሉም የአስተዳደር ሠራተኞች በስልጠናው መሳተፍ እንደሚጠበቅባችሁ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፤

  • መምህራንን በተመለከተ- በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ላይ የሚገኙ መምህራን የመሳተፍ ግዴታ የለባቸውም፡፡ ነገር ግን በአምዩ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን በስልጠናው የመሳተፍ ግዴታ አለባቸው፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ