‹‹የጥበብ ሀውልት›› (Statue of Wisdom) በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የዘንድሮ ዓመት ተመራቂ የሥነ-ህንፃ ተማሪ ያፌት ጌታሁን ተቀርፆ መስከረም 10/2010 ዓ.ም ተመርቋል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ::

ቀራፂው ተማሪ ያፌት የሀውልቱን ተምሳሌት ሲያብራራ ‹‹የዩኒቨርሲቲውን አንጋፋነትና የንባብን እሴት በአዛውንቱ ገጽታና በሚያነበው መጽሐፍ ለማሳየት ሞክሪያለሁ›› ብሏል፡፡

ሀውልቱን ለመቅረጽ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ዩኒቨርሲቲው ቢያሟላም ተማሪ ያፌት ችሎታ፣ ጉልበትና ጊዜውን ሰጥቶ የተማረውን በተግባር ማሳየቱ የሚደነቅ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ ተናግረው ተማሪው በዩኒቨርሲቲው ያኖረው የጥበብ አሻራ ሌሎች መምህራንና ተማሪዎችን በእጅጉ የሚያነሳሳ ነው ብለዋል፡፡