ለቢሮ አስተዳደሮች፣ በማዕከልና በየኮሌጁ ላሉ የእቅድ ባለሙያዎች፣ ለሬጅስትራር መረጃ ባለሙያዎች፣ በኮሌጆችና በማዕከል ላሉ የሰው ሀብት መረጃ ባለሙያዎች፣ ለካምፓስ አስተዳደሮች በመረጃ አያያዝና አስተዳደር ዙሪያ መጋቢት 17/2010 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ::

የስልጠናው ዓላማ የሰው ኃይልና ልዩ ልዩ የሥራ መረጃዎች አደረጃጀትና አጠቃቀም በማቀላጠፍና የጥራት ደረጃውን በማሳደግ ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ የመረጃ ሥርዓት እንዲኖር ማድረግ ነው ሲሉ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ትግበራ ዳይሬክቶሬት ባለሙያ አቶ ታምራት ካሳዬ ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው የመምህራን፣ የተማሪዎችና የአስተዳደር ሠራተኞች ሙሉ መረጃ በአግባቡ እንዲደራጅ የሚያደርግ፣ ለመረጃ አያያዝ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ፎርማቶችና የመረጃ ልውውጥ ሂደት ላይ ግንዛቤ የሚፈጥር፣ ወጪ ቆጣቢና ጥራት ያለው መረጃ ለተጠቃሚዎች በቀላሉ እንዲገኝና ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት መረጃን በኃላፊነትና በዕውቀት እንዲይዙ የሚያስችል እንዲሁም በዕውቀት ላይ የተመሰረተ የመረጃ አያያዝና አስተዳደርን የሚያሰፍን ነው፡፡

የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ንጉሴ ታደገ እንደገለፁት ከመረጃ ጋር ግንኙነት ያላቸው የቢሮ አስተዳደሮች በመረጃ አያያዝና አስተዳደር እንዲሁም አገልግሎትን ከማቀላጠፍ አኳያ የእንግዳ አቀባበልና የእንግሊዝኛ ቋንቋ አጠቃቀም የመሳሰሉ ስልጠናዎችን በመስጠት አቅምና ሙያቸውን አጎልብቶ የዩኒቨርሲቲውን ሥራ ማሻሻል ይቻላል፡፡