በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ የሒሳብ ትምህርት ክፍል  ኒስ ከተማ ከሚገኘው ‹‹Center Of International Pure and Applied Mathematics (CIMPA) ››  ጋር በትብብር እየሰራ ሲሆን ጥር 15/2011 ዓ/ም ለትምህርት ክፍሉ መምህራንና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ 2ኛ ዙር ሴሚናር አዘጋጅቶ ከማዕከሉ በመጡ ፕሮፌሰሮች ገለፃ ተደርጓል፡፡ ምስሉን ለማየት ከዚህ ይጫኑ

የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር የቻለ ከበደ መሰል  ሴሚናሮችን <<CIMPA>>ን ከመሰሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ማዘጋጀትና አብሮ የመሥራትሁኔታ የመማር ማስተማሩን ሥራ ከማጠናከር አንፃርና ዩኒቨርሲቲያችን የፒ ኤች ዲ ፕሮግራሞችን ለማስፋፋትና ጥራት ያለው ትምህርትን ለመስጠት እያደረገ ባለው ጥረት ውስጥ አበረታች አስተዋፅዖ ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከማዕከሉ ጋር የተጀመረውን ግንኙነት ለማጠናከርና በዘርፉ ለመሥራት ዝግጁ  መሆኑን ያረጋገጡት ም/ፕሬዝደንቱ  ከማዕከሉ ጋር ግንኙነት በመፍጠር  ልምድ ያካበቱ ፕሮፌሰሮች እንዲመጡ በማድረግ የፒ ኤች ዲ ኮርሶችን እንዲሰጡ ለማስቻል ኮሌጁ፣ የሂሳብ ትምህርት ክፍልና የትምህርት  ክፍሉ መምህር የሆኑት Dr PatricK ያሳዩት ቁርጠኝነትና አርኣያነት የሚበረታታና ለሌሎችም ጥሩ ተሞክሮ የሚሆን ተግባር ነው ብለዋል፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች ላይ ማስተማር ከምንም በላይ ያስደስተኛል ያሉት Prof. Michel Waldschmidt እስካሁን ባለው ቆይታቸው በ17 ሀገራት የተለያዩ ኮርሶችን የሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውም ከወጣት ተማሪዎች ጋር አስደሳች ጊዜን እንዳሳለፉ ገልፀው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ‹‹CIMPA›› ሊሰራበት የሚገባው ትክክለኛ ቦታ መሆኑን መገንዘባቸውንና  በቅርቡ የማዕከሉ ዳይሬክተር ወደ ዩኒቨርሲቲው ስለሚመጡ ግንኙነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡
CIMPA መቀመጫውን በፈረንሳይ ሀገር ኒስ ከተማ ያደረገና የሒሳብ ትምህርትን በአፍሪካና በታዳጊ ሀገሮች ለማሳደግ የሚሰራ ተቋም ነው፡፡

ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት