የአልሙናይ ቀን በድምቀት ሊከበር ነው!

ዩኒቨርሲቲው 3ኛውን የአልሙናይ ቀን ግንቦት 18/2011 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ ሊያከብር ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት የአልሙናይ ጉዳዮች አስተባባሪ ዶ/ር ሀብታሙ እንድሪስ እንደገለፁት  የአልሙናይ ቀን የሚከበረው ዩኒቨርሲቲው ከቀድሞ ተማሪዎቹ ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ተቋሙን በሚረዱበት እንዲሁም የአልሙናይን ምሥረታ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ለማድረግ ነው፡፡ 

ለአገራዊ ልማት የበኩላቸውን ድርሻ የሚወጡ ብቃትና ጥራት ያላቸውን ምሁራን በማፍራት 31 ዓመታትን ያስቆጠረው ዩኒቨርሲቲው ቀደም ሲል በውኃ ምርምር ዘርፍ የተጫወተው ሚና ቀላል አይደለም ያሉት ዶ/ር ሀብታሙ ለአልሙናይ መሥረታ መጠናከር እና በቀጣይ ሊከናወኑ በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ለማካሄድ በአገር ውስጥና በውጭ አገራት በተለያየ የሥራ ዘርፍ ለሚገኙ የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጥሪ ቀርቧል፡፡

የ2011 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲው ተመራቂ ተማሪዎች፣ በተለያዩ ከፍተኛ የመንግስሥት የሥራ ኃላፊነት ላይ የሚገኙ የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት የአልሙናይ ቀን የውይይት መድረክ ይሳተፋሉ፡፡

ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት