የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ት/ቤት የምርምርና ማኅበረሰብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ት/ቤት ጋር በመተባበር ከሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ፣ ከጤና ሳይንስ እና ከማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጆች የተወጣጡ መምህራን ባቀረቡት የምርምር ንደፈ ሃሳብ ላይ ኅዳር 04/2013 ዓ/ም ግምገማ አካሂዷል፡፡

የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ት/ቤት የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪ ዶ/ር ቤታ ጻማቶ እንደገለጹት የማኅበረሰቡን ችግር በሳይንሳዊ መንገድ መፍታት የሚችሉ የምርምር ንድፈ ሃሳቦችን ገምግሞ ለማሳለፍ መድረኩ ተዘጋጅቷል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የሥነ-ትምህርት፣ ሳይኮሎጂ፣ ልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት እንዲሁም የጎልማሳ ትምህርትና የማኅበረሰብ እድገት የትምህርት ክፍሎች በግምገማው የተሳተፉና 9 የምርምር ንድፈ ሃሳቦች ለግምገማ የቀረቡ ሲሆን ‹‹Normative beliefs about Aggression as predictor of Aggressive and Fighting Behaviors among High School Students››፣ ‹‹Indigenous Knowledge Transfer Methods of Weaver Community in Gamo Zone: Implication for Adult Education and Community Development››፣ ‹‹Psychological Crisis and Associated Factors among High School Students in the Era of COVID-19 in Sawla Town of Gofa Zone, Southern Ethiopia›› የሚሉት ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ት/ቤት ዲን አቶ አንለይ ብርሃኑ በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ሥር በዓመት ሁለት ዙር ጥሪ ተደርጎ የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተቀራራቢ ሙያ ባላቸው ሌሎች መምህራን የጥናትና ምርምር ንድፈ ሃሳብ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፡፡ በግምገማው የተሻለ ውጤት ያመጡ ንድፈ ሃሳቦች የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እና ካለው በጀት አኳያ በዩኒቨርሲቲው የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ተናግረዋል፡፡