የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ የዩኒቨርሲቲውን ምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝደንት ከዩኒቨርሲቲው መምህራን መካከል አወዳድሮ ለመመደብ ይፈልጋል፡፡ አመልካቾች የትምህርት ደረጃቸው 2ኛ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከማመልከቻቸው ጋር ቀጥሎ የተዘረዘሩ ማስረጃዎችን በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. Curriculum vitae (CV)
  2. የትምህርት ደረጃን የሚገልጽ ሰርቲፊኬት አንድ ፎቶ ኮፒ
  3. የአካዳሚክ ማዕረግ የሚገልጽ ደብዳቤ
  4. በዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ወይም በምርምር ተቋም በተመራማሪነት ያገለገሉበትን ጊዜ የሚገልጽ ደብዳቤ
  5. በዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉበትን ጊዜ የሚገልጽ ደብዳቤ
  6. በዩኒቨርሲቲው በምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝደንትነት ቢመደቡ የዘርፉን ሥራ ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂክ ዕቅድ በዝርዝር ማቅረብ የሚችል/ትችል የሆናችሁና

ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ከኅዳር 11/2013 እስከ ኅዳር 24/2013 ዓ.ም በሥራ ሰዓት ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ቦርዱ ይገልጻል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት