የጤና ሚኒስቴር ልዑካን ቡድን ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና ከጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ባለድርሻ አካላት ጋር የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ አፈፃፀምን ታኅሣሥ 16/2013 ዓ/ም ጎብኝቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ


የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝደንት ወ/ሮ ታሪኳ ወ/መድኅን በጉብኝቱ ወቅት ገለጻ ሲያደርጉ የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ ሂደቱ በሒሳብ ስሌት 80 በመቶ እና በአፈፃፀም ደረጃ 85 በመቶ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ከወሰን ጋር ተያይዞ የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ከይዞታቸው ለተነሱ 26 ሰዎች ተተኪ ቦታ ለመስጠት ዩኒቨርሲቲው ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደርና ከማዘጋጃ ቤት ጋር በጋራ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡

የአጥርና የግቢ ውበት ሥራዎችን በማጠናቀቅ እንዲሁም የሕክምናና የውስጥ ቁሳቁሶችን በማሟላት በ2014 ዓ/ም በከፊል የአገልግሎትና የማስተማር ሥራ ለመጀመር መታቀዱንም ወ/ሮ ታሪኳ ገልጸዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት