ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2012 መደበኛ 1ኛ ዓመት ተማሪ የነበራችሁና በ1ኛ ሴሚስተር ውጤታችሁ 1.0 ነጥብና በላይ እንዲሁም ከ2.00 ነጥብ በታች ላመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ

በኮቪድ-19 ምክንያት የተቋረጠው የ2012 ዓ.ም የ2ኛ ሴሚስተር ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ‘Fʼ and ʻD’ ውጤት ለማሻሻል ቲዩቶሪያል ትምህርት በማካሄድ ድጋሚ የመፈተን ዕድል ለመስጠት ዩኒቨርሲቲው ስላቀደ የ2012 1ኛ ዓመት ተማሪ የነባራችሁና የሴሚስተር ውጤታችሁ 1.0 ነጥብና በላይ እንዲሁም ከ2.00 ነጥብ በታች ያመጣችሁ ተማሪዎች ከየካቲት 1-2/2013 ዓ/ም ድረስ

  • የጫሞ ካምፓስ ተማሪዎች በጫሞ ካምፓስ
  • የዓባያና የነጭ ሳር ካምፓስ ተማሪዎች በዓባያ ካምፓስ
  • የዋናው ግቢና የኩልፎ ካምፓስ ተማሪዎች በዋና ግቢ
  • የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎች በሳውላ ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ እያሳሳብን
  • ቲዩቶሪያል የሚሰጥበት ቀን ከየካቲት 3-9/2013 ዓ.ም ሲሆን
  • ፈተና የሚሰጥበት ቀን ከየካቲት 10-13/2013 ዓ.ም ድረስ መሆኑን እንዲሁም
  • የኮርስ ምርጫ ዶርም ስትወስዱ እንደገና የምታካሂዱ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • መምጣት የሚገባችሁ ተማሪዎች ስም ዝርዝር በዩኒቨርሲቲው ቴሌግራም የተለቀቀ ሰለሆነ በማስፈንጠሪያው እንድታረጋግጡና ስማችሁ ያለው ብቻ የምትስተናገዱ ይሆናል፡፡
  • በጉዞ ወቅትና ወደ ካምፓስ ስትገቡ ለኮሮና ቫይረስ ጥንቃቄ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መጠቀም ይጠበቅባችኋል፡፡
  • ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት