‹‹የጠራ የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ዕቅድ፣ ፕሮግራሞችና ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ግንዛቤና ትግበራ ለኢትዮጵያ ዕደገት፣ ልማትና ብልፅግና›› በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 10/2013 ዓ/ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢና ሳውላ ካምፓስ ከሚገኙ የካውንስል አባላትና ሠራተኞች ጋር የአሠልጣኝነት ሥልጠናዊ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ፕሮግራም፣ የከፍተኛ ትምህርት የ10 ዓመት ፍኖተ ካርታ፣ የሳይንስ ፖሊሲና ስትራቴጂ እና የሳይንስ ንዑስ ዘርፍ የ10 ዓመት ፍኖተ ካርታ፣ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ቁልፍ የተግባር አፈፃፀም አመላካቾች (KPIs)፣ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቅበላና ምደባ ፖሊሲ የሚሉት በሥልጠናዊ ውይይቱ ቆይታ እየተዳሰሱ የሚገኙ ዋና ዋና ነጥቦች ሲሆኑ በሰነዶቹ ላይም የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች እየቀረቡ በውይይቱ እንዲዳብሩ እየተደረገና የጠራ ግንዛቤ እንዲኖርም ምላሾች እየተሰጡ ናቸው፡፡

በሥልጠናው የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች አሠልጣኝ ሲሆኑ ዲኖች፣ የአካዳሚክና አስተዳደር ዘርፍ ዳይሬክተሮች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ የሥራ አስተባባሪዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት እየተሳተፉ ናቸው፡፡

ሥልጠናዊ ውይይቱ ከሰኞ መጋቢት 13/2013 ዓ/ም ጀምሮ በኢንስቲትዩት፣ ኮሌጆች፣ ት/ቤቶችና የተለያዩ የሥራ ዘርፎች ደረጃ ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ እንዲደርስ የሚደረግ ይሆናል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት