ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ በክረምትና በርቀት የትምህርት ፕሮግራሞች መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን በአርባምንጭና በሳውላ ካምፓስ ተቀብሎ በመጀመርያ ዲግሪ ከ2011 ዓ.ም ከሐምሌ ወር ጀምሮ ማሰልጠን ይፈልጋል::

Read more: ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

 

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት ለ2011 የትምህርት ዘመን በክረምት መርሐ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል:: 

Read more: ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

በከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት አዲስ የመምህራን ልማት መመሪያ ተዘጋጅቶ ውይይት እየተደረገበት ነው

በከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የመምህራን ልማት ረቂቅ መመሪያ ላይ ግንቦት 8/2011 ዓ/ም ክላስተራዊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር የቻለ ከበደ እንደገለጹት ረቂቅ መመሪያው የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሰጠው ኃላፊነት መሠረት የተዘጋጀ ሲሆን በረቂቅ መመሪያው ላይ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ውይይቶች ተደርገውበት አሁን ላይ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በክላስተር እየተወያዩበት ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ቀደም ወጥ የሆነ መመሪያ ባለመኖሩ ምክንያት ሲፈጠሩ የነበሩ ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ መመሪያው ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ እንደሚጠበቅና ከውይይቶቹ በኋላ ማስተካከያዎች ተካተው ተግባራዊ እንደሚደረጉ ዶ/ር የቻለ ተናግረዋል፡፡ ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

Read more: በከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት አዲስ የመምህራን ልማት መመሪያ ተዘጋጅቶ ውይይት እየተደረገበት ነው

 

በህግ የበላይነትና በህገ-መንግሥት እንዲሁም ፌዴራሊዝምና አገረ-መንግሥት ግንባታ ላይ ስልጠና ተሰጠ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ከደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጋር በመተባበር ‹‹በህግ የበላይነትና ህገ-መንግሥት›› እንዲሁም ‹‹ፌደራሊዝምና ሀገረ-መንግሥት ግንባታ›› በሚል ርዕስ ከግንቦት 5-6/2011 ዓ/ም ድረስ ለፍትህ አካላትና ባለ ድርሻ አካላት ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

Read more: በህግ የበላይነትና በህገ-መንግሥት እንዲሁም ፌዴራሊዝምና አገረ-መንግሥት ግንባታ ላይ ስልጠና ተሰጠ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ONLINE እና በE-LEARNING የታገዘ ትምህርት ለመስጠት ምዝገባ ጀመረ

ዩኒቨርሲቲው ONLINE እና በE-LEARNING የታገዘ ትምህርት ለመስጠት ከ Lucy Consulting Engineers PLC (LUCY) ጋር የመግባቢያ ስምምነት በተፈራረመው መሠረት ትምህርቱን ለማስጀመር ምዝገባ መጀመሩ ተገለፀ፡፡ በፕሮግራሙ አጀማመርና አጠቃላይ ሁኔታ ዙሪያ ከኮሌጅ፣ ትምህርት ቤትና ፋካልቲ ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር  ግንቦት 6/2011 ዓ/ም ውይይት ተካሂዷል፡፡ ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ONLINE እና በE-LEARNING የታገዘ ትምህርት ለመስጠት ምዝገባ ጀመረ