በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ የጌጣጌጥ ማዕድናት ምርትና ግብይት ዘርፍ ለባለድርሻ አካላት ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫና የምክክር መደረክ ላይ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በኮንሶና ደቡብ ኦሞ ዞኖች የማዕድን አለኝታ ጥናት ማካሄዱ ተገልጿል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲንና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር ፈቃዱ ማሴቦ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ዩኒቨርሲቲ ኖርዌይ ከሚገኘው በርጌን ዩኒቨርሲቲ ጋር እየሠራ የሚገኘው የፕሮጀክት ሥራ በመጀመሪያ ዙር አመርቂ ውጤት በማስመዝገቡ ዩኒቨርሲቲው ለ2ኛ ዙር የʻNorwegian Program for Capacity Development in Higher Education and Research for Development/NORHEDʼ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ሆኗል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ዩኒቨርሲቲው ለ7ኛ ጊዜ ያሠለጠናቸውን 87 የሕክምና ዶክተሮች ታኅሣሥ 24/2013 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 32ቱ ሴቶች ናቸው፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወደ ሀገራችን ከገባበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ሌሎች የሀገሪቱ የጤና ባለሙያዎች ሁሉ የዩኒቨርሲቲያችን የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራንና የዛሬ ተመራቂ ዶክተሮች ወረርሽኙን ለመከላከል ግንዛቤ በማስጨበጥ እንዲሁም ለኅብረተሰቡ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ያለ እረፍት ሲያገለግሉ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ሂደት በኮቪድ-19 በሽታ ተይዘው ከዳኑት መካከል መምህራንና ተመራቂ ተማሪዎች ይገኙበታል ብለዋል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ7ኛ ዙር ያሠለጠናቸውን 87 የሕክምና ዶክተሮችን በመጪው ቅዳሜ ታኅሣሥ 24/2013 ዓ/ም በድምቀት ያስመርቃል፡፡ ከተማራቂዎቹ መካከል 32ቱ ሴቶች ሲሆኑ 55ቱ ወንዶች ናቸው፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከIBRO እና DANA ፋውንዴሽኖች ጋር በመተባበር የአንጎል ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንትን ምክንያት በማድረግ ለኮሌጁ መምህራን፣ ተመራማሪዎችና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች እንዲሁም ለመሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከታኅሣሥ 12-16/2013 ዓ.ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ የአዕምሮ ጤና ምንነት፣ የአዕምሮ ጤና እድገት እና የአዕምሮ ጤናን የሚጎዱ ሱሶችና አደንዛዥ ዕጾች የሥልጠናው ይዘቶች ናቸው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ