የአርባ ምንጭ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ ለመጡ ባለሙያዎች ምርትና ምርታማነትን መደገፍ በሚያስችሉ የግብርና ቴክኖሎጂና ሞዴሎች ዙሪያ “Decision Support System for Agro-technology Transfer/DSSAT” በሚል ርዕስ ከሚያዝያ 16-19/2016 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ የእምነቱ ተከታይ ለሆኑ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ እንዲሁም የቀድሞ ምሩቃን እንኳን ለስቅለትና ትንሣኤ በዓላት በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የፍቅር እንዲሆን ከወዲሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡

የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን በ2016 ዓ.ም የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶችን ለሁሉም ህጋዊ አቅራቢዎች/ነጋዴዎች/ተደራሽ ለማድረግ፣ የተቋማት ብልሹ አሠራሮችን ለመከላከል እንዲሁም ሁሉንም አቅራቢዎች/ነጋዴዎች እኩል ለማሳተፍ የግዥ ሥርዓቱን በማዘመን ግልፅና ቀልጣፋ አሠራር በመዘርጋት ማንኛውም ግዥ በኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሥርዓት “eGP/electronic Government Procurement” ብቻ እንዲፈፀም መወሰኑ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሠረት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ማንኛውንም ግዥ በኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሥርዓት /eGP/ ለመፈፀም ሙሉ በሙሉ ሥርዓቱን በመዘርጋት ተግባራዊ በማድረግ ላይ የሚገኝ በመሆኑ በአርባ ምንጭ ከተማና ዙሪያው የምትገኙ አቅራቢ ህጋዊ ነጋዴዎች በመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ኤጀንሲ ምዝገባ በማድረግ በኤጀንሲ ድኅረ ገጽ ላይ በሚለቀቁ ግዥዎች ላይ እንድትሳተፉ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ፈጠራ ልማት ማበልጸጊያ ማዕከል የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር ላሸነፉ ተማሪዎች ሽልማት እና በዕውቅ የሥራ ፈጠራ አማካሪና ደራሲ ቁልፍ መልእክት የማስተላለፍ መርሃ ግብር ሚያዝያ 17/2016 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሀገር በቀል ዕውቀት ለሥራ ፈጠራ፣ ለቁጠባና ለዘላቂ ሰላም በሚል ርእስ ሀገር አቀፍ የምርምር ዐውደ ጥናት ሚያዝያ 19/2016 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡