Print

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ከአግታ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ጋር በመተባበር ከጠቅላላ አገልግሎትና አውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ ፋከልቲ ለተወጣጡ ባለሙያዎችና መምህራን በተሽከርካሪዎች አያያዝ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የዩኒቨርሲቲው የጠቅላላ አገልግሎት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዓለማየሁ ወልዴ እንደገለጹት ብዙ ችግሮችን ሊያመጡ በሚችሉ የመኪና አያያዝ ጉዳዮች ዙሪያ በትኩረት በመሥራት የመኪናዎችን የአገልግሎት ዘመን ማራዘም እንደሚቻል ጠቅሰው ሥልጠናው የዘርፉ ባለሙያዎች መኪናዎችን በጥንቃቄ በመያዝና በመጠገን የድርሻቸውን በመወጣት በተሸከርካሪዎች ላይ በጥንቃቄ ጉድለት የሚደርሰውን ጉዳት እንዲቀንሱ ያስችላል ብለዋል፡፡

የአግታ ካምፓኒ የአውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግና ሜይንተናንስ ትምህርት ክፍል ማኔጀር አቶ ሀድጎ ፀሐዬ በበኩላቸው የተለያዩ ቅድመ ጥገናዎችን ማድረግ መኪኖች ለረዥም ጊዜ ጤናማ እንዲሆኑና እንዲሁም ጤንነቱ የተጠበቀ የሰው ኃይል እንዲኖር ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የተሸከርካሪዎች ጥገና ክፍል አስተባባሪ አቶ አዲሱ ገሌ የቅድመ መከላከል ሥልጠናው ያለንን ግብዓት በአግባቡ ለመጠቀምና ተሽከርካሪዎች የረዥም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ አኳያ መሰል አጫጭር ሥልጠናዎች የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ የሚኖራቸው ሚና የጎላ ይሆናል፡፡

ሠልጣኞች በሰጡት አስተያየት ሥልጠናው በተሽከርካሪ አያያዝ ዙሪያ ያላቸውን የግንዛቤ ክፍተት እንደቀረፈላቸውና በቀጣይም በተለይ የመኪና ሞተር ችግር ከመድረሱ በፊት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ባለመዘናጋት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ያስገነዘባቸው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

                                                                                                                                                   የብሩህ ተስፋ ማዕከል!    
                                                                                                                                         የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት