Print

በ2014 የትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ የ12 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው ለአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ትምህርት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቅበላ ቀን የካቲት 29/2015 ዓ/ም፣ የምዝገባ ቀን የካቲት 30 እና መጋቢት 01 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን መጋቢት 04 ቀን 2015 ዓ.ም ይሆናል፡፡ ስለሆነም የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ትምህርት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን ወደዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡-   

 

በመያዝ ዓባያ ካምፓስ የተመደባችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ (ዓባያ ግቢ)፣ ጫሞ ካምፓስ የተመደባችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው ጫሞ ካምፓስ፣ ሳውላ ካምፓስ የተመደባችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እና የአቅም ማሻሻያ ትምህርት እንድትጀምሩ እያሳሰብን ስለተመደባችሁ ካምፓስ፣ መማሪያ ክፍል (Section) እና የተማሪ መለያ መታወቂያ ቁጥር (Student Number) ዝርዝር መረጃ ከዩኒቨርሰቲው ድረ-ገጽ www.amu.edu.et እና ቴሌግራም https://t.me/arbaminch_university/10022 እና https://t.me/arbaminch_university/10025 ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

 ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናስታውቃለን፡፡

 የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት