በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮሎጂ ት/ክፍል በባዮቴክኖሎጂ ትምህርት ፕሮግራም የ3 ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ብርሃኑ ገመዳ መጋቢት 22/2015 ዓ/ም ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ የ3 ዲግሪ ማጠናቀቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዓባያ ካምፓስ በአዲሱ አስተዳደር ሕንፃ አዳራሽ ያቀርባል፡፡

ዕጩ ዶ/ር ብርሃኑ ገመዳ በኮሌጁ ታሪክ የመጀመሪያው የባዮቴክኖሎጂ የ3 ዲግሪ ምሩቅ ሲሆን ‹‹Characterization of Bacteria Causing Ensete [Ensete ventricosum (Welm.) Cheesman] Wilt Disease and its Management Strategies in Gamo Highlands of Ethiopia›› በሚል ርዕስ ያከናወነውን የመመረቂያ ጥናት ጽሑፍ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት