ወ/ሮ ድርሻዬ አድማሱ አላሆ ከአባታቸው አቶ አድማሱ አላሆ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ትርፍነሽ ሞገስ በአርባ ምንጭ ከተማ ታኅሣሥ 24/1984 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

ወ/ሮ ድርሻዬ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ እንዲሁም የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃና መሠናዶ ት/ቤት አጠናቀዋል፡፡

ወ/ሮ ድርሻዬ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በአካውንቲንግና ፋይናንስ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በ2013 ዓ/ም አግኝተዋል፡፡

ወ/ሮ ድርሻዬ ከጥር 1/2008 - ሰኔ 30/2008 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሣውላ ካምፓስ በተማሪዎች አገልግሎት የምግብ ቤት ጽዳት ሠራተኛ፣ ከሐምሌ 1/2009 – 2011 ዓ/ም በሣውላ ከምፓስ ቤተ-መጽሐፍት በር ፈታሽ፣ ከሚያዝያ 1/2011 ዓ/ም - ግንቦት 30/2013 ዓ/ም በሣውላ ካምፓስ የሕሙማን ረዳት እንዲሁም ከሰኔ 1/2013 ዓ/ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ዕለት ድረስ በኩልፎ ካምፓስ ክሊኒክ የሕሙማን ረዳት በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ወ/ሮ ድርሻዬ ባለትዳር ሲሆኑ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ31 ዓመታቸው ግንቦት 10/2015 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በወ/ሮ ድርሻዬ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት