አቶ ፍሬው ዳንኤል ከአባታቸው ከአቶ ዳንኤል ሻሌ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አማረች ጸላ በቀድሞው ጋሞ ጎፋ አውራጃ አርባ ምንጭ ወረዳ ቆላ ሼሌ ቀበሌ በ1976 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በኩልፎ 1ና መለስተኛ 2 ደረጃ ት/ቤት እና የ2 ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ 2 ደረጃና መሠናዶ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡

አቶ ፍሬው በአርባ ምንጭ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ በአውቶሞቲቭ ኤሌክትሪሲቲ/ኤሌክትሮኒክስ በደረጃ-4 ሰኔ 2002 ዓ/ም ያጠናቀቁ ሲሆን በትራንስፖርት ሚኒስቴር የአሽከርካሪዎችና ሜካኒኮች ማሠልጠኛ ማዕከል በአሽከርካሪዎች አሠልጣኝነት፣ ፈታኝነትና ተሽከርካሪዎች መርማሪ ቴክኒሻንነት በደረቅ 1 ሠልጥነው ጥር 03/2005 ዓ/ም የምስክር ወረቀት አግኝተዋል፡፡

አቶ ፍሬው ዳንኤል ከጥር 11/1999 - መስከረም 2004 ዓ/ም በዩናይትድ ጋራዥ ረዳት ሜካኒክ፣ ከጥር 01/2005 - ሰኔ 30/2005 ዓ/ም በመገናኛ የአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ተቋም በደረቅ-1 የንድፈ ሃሳብና የተግባር አሠልጣኝ፣ ከሐምሌ 1/2005 - ታኅሣሥ 30/2006 ዓ/ም በፊውቸር ላይት የአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ተቋም የደረቅ-1 አሠልጣኝ፣ ከመጋቢት 29/2006 - ሚያዝያ 13/2007 በሰገን አ/ሕ/ዞን አሌ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የአምቡላንስ ሾፌር፣ ከነሐሴ 20/2007 - ታኅሣሥ 12/2009 ዓ/ም በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከፍተኛ የደረቅ ጭነት ሾፌር እና ከታኅሣሥ 13/2009 - ጳጉሜ 02/2009 ዓ/ም በ‹‹SINOHYDRO›› ኮርፖሬሽን መንዲር-ሃና መንገድ ፕሮጀክት የፒክ አፕ መኪና ሾፌር በመሆን አገልግለዋል፡፡

አቶ ፍሬው ግንቦት 01/2010 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በእጥ-8 የሥራ መደብ በጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በደረጃ -ⴸ ሾፌር በመሆን በቋሚነት የተቀጠሩ ሲሆን ሕይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ በዳይሬክቶሬቱ በደረጃ-VIII የከባድ መኪና ሾፈር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ አቶ ፍሬው በሥራ በቆዩባቸው ዓመታት ከሠሩባቸው ተቋማት የተለያዩ የምስጋና ምስክር ወረቆቶችን አግኝተዋል፡፡

አቶ ፍሬው በደረሰባቸው ድንገተኛ ህመም በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል እና በወላይታ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሐምሌ 12/2015 ዓ/ም በ39 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ አቶ ፍሬው ዳንኤል ባለ ትዳርና የ2 ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአቶ ፍሬው ዳንኤል ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት