መምህር ሀብታሙ ሻቴ ከአባታቸው አቶ ሻቴ ዮሻ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ባዩሽ በቀለ ታኅሣሥ 19/1972 ዓ/ም በቀድሞው ጋሞ ጎፋ አውራጃ ካምባ ወረዳ ተወለዱ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በካምባ ባዮ 1 ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም የ2 ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2 ደረጃ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡

መ/ር ሀብታሙ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በባዮሎጂ የትምህርት መስክ ሐምሌ 15/ 1998 ዓ/ም ዲፕሎማ እና ሰኔ 23/2003 ዓ/ም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን 2 ዲግሪያቸውን በ‹‹Watershed Management›› ከጂማ ዩኒቨርሲቲ ኅዳር 4/2007 ዓ/ም አግኝተዋል፡፡ መ/ር ሀብታሙ የ3 ዲግሪ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹Biodiversity Conservation Management›› በመከታተል ላይ ነበሩ፡፡

መ/ር ሀብታሙ ከመስከረም 1/1999 ዓ/ም - የካቲት 30/2000 ዓ/ም በምዕራብ ዓባያ ወረዳ በመምህርነት ያገለገሉ ሲሆን የካቲት 12/2000 ዓ/ም አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን ተቀላቅለው እስከ የካቲት 11/2011 ዓ/ም በአፕላይድ ባዮሎጂ ቤተ ሙከራ ቴክኒካል ረዳት I፣ ከየካቲት 12/2001 ዓ/ም - የካቲት 11/2003 ዓ/ም ቴክኒካል ረዳት II፣ ከየካቲት 12/2003 ዓ/ም - ጳጉሜ 4/2003 ዓ/ም ቴክኒካል ረዳት III፣ ከጳጉሜ 5/2003 ዓ/ም - ጳጉሜ 4/2004 ዓ/ም ረዳት ምሩቅ I፣ ከጳጉሜ 5/2004 ዓ/ም - ኅዳር 3/2007 ዓ/ም ረዳት ምሩቅ II እንዲሁም ከኅዳር 4/2007 ዓ/ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በሌክቸረር አካዳሚክ ማዕረግ ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ በተጨማሪም መ/ር ሀብታሙ ከጥቅምት 30/2010 ዓ/ም - ግንቦት 30/2011 ዓ/ም ድረስ በግብርና ሳይንስ ኮሌጅ የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ት/ክፍል ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡

መ/ር ሀብታሙ ባለትዳር እና የሦስት ወንድና የሁለት ሴት ልጆች አባት ሲሆኑ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሐምሌ 25/2015 ዓ/ም በ43 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመምህር ሀብታሙ ሻቴ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

 

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት