በ2012 እና 2013 የትምህርት ዘመን ባጋጠመን የኮቪድ-19 (ኮሮና ቫይረስ) ወረርሽን ምክንያት መደበኛ የትምህርት ካላንደር መዛባቱ ይታወቃል፡፡ በወረርሽኙ ምክንያት የተከሰተውን የትምህርት ጊዜ ብክነት በማስተካከል ላይ የምንገኝ በመሆኑ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ባች (3 ዓመት ቅድመ ምረቃ) ተማሪዎች ቅበላ፣ ምዝገባ እና ትምህርት የሚጀመርበት ቀን በልዩ ሁኔታ በጊዜ እንዲሆን ተወስኗል፡፡

 በዚህም መሠረት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 2013 ባች (3 ዓመት ቅድመ ምረቃ) ተማሪዎች፡-

1ኛ.  የቅበላ ቀን፦ ሐሙስ መስከረም 3 ቀን 2016 ዓ/ም፣

2ኛ.  የምዝገባ ቀን፦ ዓርብ መስከረም 4 ቀን 2016 ዓ/ም፣ እና

3ኛ.  ትምህርት የሚጀመርበት ቀን፡- ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ/ም

መሆኑን በአጽንዖት እየገለጽን ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማይቀበል መሆኑን እንዲሁም ምዝገባ የሚፈፀመው በአካል በመገኘት መሆኑን ያሳውቃል።

 

 የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት

 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

 

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት