በአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ‹‹Water Resource and Irrigation Engineering›› ፋከልቲ በ‹‹Irrigation and Drainage Engineering›› ትምህርት ፕሮግራም ላላፉት አምስት ዓመታት የ3 ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር አበራ ሽጉጤ የምርምር ሥራውን ነሐሴ 26/2015 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርቧል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ዕጩ ዶ/ር አበራ የመመረቂያ ጽሑፉን ‹‹Analysis of Rainfall-runoff, Evapotranspiration, Ground Water Recharge and Storage Anomalies under Climate Change and Anthropogenic Stresses in Bilate Sub-Basin, Ethiopia›› በሚል ርእስ ያከናወነ ሲሆን የመመረቂያ ጽሑፉ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

ዕጩ ዶ/ር  አበራ ሽጉጤ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹Soil and Water Engineering›› በ2002 ዓ/ም እና 2 ዲግሪውን ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹Irrigation and Drainage Engineering›› በ2008 ዓ/ም ያጠናቀቀ ሲሆን የ3 ዲግሪ ትምህርቱን ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ‹‹Water Resource and Irrigation Engineering›› ፋከልቲ በ‹‹Irrigation and Drainage Engineering›› ትምህርት ፕሮግራም ሲከታተል ቆይቷል፡፡

በግምገማ መርሃ ግብሩ ፕ/ር ጤናዓለም አየነው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ዶ/ር ፋሲካው አጥናው ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በውጭ ገምጋሚነት እንዲሁም ዶ/ር አብደላ ከማል በውስጥ ገምጋሚነት የተሳተፉ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር፣ የፋከልቲ ዲኖች፣ የዘርፉ መምህራን፣ ተመራማሪዎች እና የ2ና የ3 ዲግሪ ተማሪዎች ታድመዋል፡፡

ዕጩ ዶ/ር  አበራ ሽጉጤ የዶክትሬት ዲግሪውን በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ከጸደቀ በኋላ የሚያገኝ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት