የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ትምህርት ቤት በ2016 የትምህርት ዘመን በመደበኛ፣ በማታ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብሮች መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ከሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት በኩል በአካል እንዲሁም በመረጃ መረብ https://forms.gle/vG9KfojLfCXkgZYU9 በኩል ምዝገባ መፈጸሙ ይታወቃል፡፡


በዚህ መሠረት ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር ከዩኒቨርሲቲው ድረ ገጽ (www.amu.edu.et) እና ኦፊሻል ቴልግራም (https://t.me/arbaminch_university) ማግኘት የምትችሉ ሲሆን አመልካቾች ከትምህርት ሚኒስቴር በተላለፈው መመሪያ መሠረት የሚከተሉትን ጉዳዮች ማወቅና መተግበር የሚጠበቅባችሁ መሆኑን ከወዲሁ አጥብቀን እያሳወቅን፡-

1. የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው ከመስከረም 21 እስከ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በበይነ-መረብ የሚሰጥ መሆኑን፣
2. ሁሉም ተፈታኞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው Graduate Admission Testing (GAT) የመመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et ከመስከረም 11 እስከ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ
   ብቻ በበይነ-መረብ ማመልከት የሚገባቸው መሆኑን፣
3. ተፈታኞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና (GAT) የመመዝገቢያ ፖርታል ገብተው ሲያመለክቱ የመፈተኛ ጣቢያቸውን (ዩኒቨርሲቲ) እና ሌሎች መረጃዎችን በትክክል ተጠንቅቀው መሙላት የሚጠበቅባቸው መሆኑን፣
4. ተፈታኞች በGAT የመመዝገቢያ ፖርታል ገብተው ሲሞሉና ሲያመለክቱ ፈተናውን ለመውሰድ የሚያስፈልገውን ክፍያ ብር 1000.00/አንድ ሺህ ብር/ በቴሌ ብር አካውንት በኩል ብቻ የሚከፍሉ በመሆኑ ከወዲሁ የቴሌ ብር አካውንት
    መክፈት እና ዝግጁ ማድረግ የሚጠበቅባቸው መሆኑን፣
5. ተፈታኞች የፈተና ፕሮግራሞችና ተያያዥ መረጃዎችን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ-ገጽና ፖርታል www.aau.edu.et እና https://portal.aau.edu.et እንዲሁም ኦፍሻል የቴሌግራም ቻናል ማግኘት የምችሉ መሆኑን፣
6. በየትኛውም የመፈተኛ ማዕከላት ለፈተና ለመቀመጥና ፈተናውን ለመውሰድ ተፈታኞች ፎቶዋቸው ያለበትን Test Admission Ticket (TAT) ከ (http://portal.aau.edu.et/web/applyForAdmission/TestTaker)
    አውርደው እና ፕሪንት አድርገው መያዝ የሚጠበቅባቸው መሆኑን፣
7. የፈተና ውጤት ተፈታኞች ፈተናቸውን ሲጨርሱና በመጨረሻ መልሳቸውን ሲያስገቡ ወዲያውኑ ማየት የሚችሉ መሆኑን፣
8. የመግቢያ ፈተና የማለፍያ ነጥብ በትምህርት ሚኒስቴር የሚወሰን መሆኑን፣
9. በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲዎች የማይቀበሉ መሆኑን እና
10. ማንኛውም የመግቢያ ፈተና ያለፈ አመልካች ኦፊሻል ትራንስክሪፕት /Official Transcript/ ከቀድሞ ተቋሙ በፖስታ ሳጥን ቁጥር 21 ወይም በዩነቨርሲቲው ኦፍሻል መቀበያ ኢሜል This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. በኩል ከምዝገባ ወቅት
     ጀምሮ እስከ 60 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ ማቅረብ የሚጠበቅበት መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት