በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ትምህርት መስኮች የ3 ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የስምንት 3 ዲግሪ ተማሪዎች መመረቂያ ጽሑፎች ከሰኔ 19-21/2016 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ተገምግሟል፡፡ የ8ቱም ዕጩ ዶክተሮች መመረቂያ ጽሑፎች አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላታቸው በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝተው ጸድቀዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ዕጩ ዶ/ር ክብረአብ አዳነ ከ«Computing and Software Engineering Faculty» በ«Computing and Information Technology» ትምህርት ፕሮግራም፣ ዕጩ ዶ/ር ስለሺ ጎኔ እና  ዕጩ ዶ/ር ገብሬ የሺዋስ ከሂሳብ ት/ክፍል በ«Algebra» ትምህርት ፕሮግራም፣ ዕጩ ዶ/ር ዘውዴ ዓለማየሁ ከ«Geography and Environmental Studies» ትምህርት ክፍል በ«Environment and Natural Resource Management» ትምህርት ፕሮግራም፣ ዕጩ ዶ/ር ሮባ ጂሶ ከእንስሳት ሳይንስ ት/ክፍል በ«Animal Production» ትምህርት ፕሮግራም፣ ዕጩ ዶ/ር ነብዩ ማሴቦ ከባዮሎጂ ት/ክፍል በ«Biodiversity Conservation and Management» ትምህርት ፕሮግራም፣ ዕጩ ዶ/ር ባሮ በየነ ከኢኮኖሚክስ ት/ክፍል በ«Development Economics» ትምህርት ፕሮግራም እና ዕጩ ዶ/ር እሸቱ ቢጪሳ ከ«Geography and Environmental Studies» ትምህርት ክፍል በ«Disaster Risk Management» ትምህርት ፕሮግራም የመመረቂያ ጽሑፋቸው የተገመገሙ ተማሪዎች ናቸው፡፡

የዕጩ ዶክተሮቹ ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ የሚመረቁ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት