• የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ በዓል

 • የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 87 የሕክምና ዶክተሮችን በመጪው ቅዳሜ ያስመርቃል

 • 33rd virtual graduation ceremony for Master and Undergraduate students on 5th Sept.

 • አርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ለ33ኛ ጊዜ ሊያስመርቅ ነው

 • Welcome to Arbaminch University

 • ዩኒቨርሲቲው 140 የሕክምና ዶክተሮችን ሊያስመርቅ ነው

 • 6th batch Medical Doctors graduation

 • ICT In education-university school partnership project

 • አንድ ቅዳሜን ለህዝቤ

 • አቶ ኦባንግ ሜቶ በዩኒቨርሲቲያችን ተገኝተው ለተማሪዎቻችን በአገራዊ አንድነት፣ የሠላምና የመቻቻል እሴት ግንባታ ዙሪያ የማነቃቂያ ንግግር ያደርጋሉ

 • 5th batch of Doctors of Medicine to be graduated on 1st December

 • Happy New Year, 2011 E.C

 • Welcome to Arba Minch University!

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

Saturday, 21 November 2020 09:59

ዩኒቨርሲቲው በሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን ላይ ሕግ የማስከበር እርምጃ እየወሰደ ለሚገኘው የሀገር መከለከያ ሠራዊት ከተቋሙ የ3 ሚሊየን ብር፣ ከመምህራንና የአስተዳደር ኃላፊዎች ከደመወዛቸው 50 በመቶ እና ከአስተዳደር ሠራተኞች እንዲሁ ከደመወዛቸው 30 በመቶ ድጋፍ እንዲደረግ ወስኗል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ የሀገሪቱ አለኝታና ጠባቂ በሆነው የሀገር መከለከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመውን አሳፋሪ ጥቃት ተከትሎ መንግሥት በሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን ላይ እየወሰደ ያለውን ሕግ የማስከበር እርምጃ በመደገፍ ከዩኒቨርሲቲው 3 ሚሊየን ብር፣ ከመምህራንና የአስተዳደር ኃላፊዎች ከደመወዛቸው 50 በመቶ እና ከአስተዳደር ሠራተኞች ከደመወዛቸቸው 30 በመቶ ድጋፍ እንዲደረግ የዩኒቨርሲቲው ካውንስል መወሰኑን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም በዩኒቨርሲቲው ሁሉም ካምፓሶች ለሠራዊቱ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ከሰኞ ኅዳር 14/2013 ዓ/ም ጀምሮ ይካሄዳል ብለዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፉን የጂ አይ ኤስ (GIS) ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ አከበረ

Saturday, 21 November 2020 09:51

የዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብ ኮሌጅ ከጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል ጋር በመሆን ዓለም አቀፉን የጂ አይ ኤስ ቀን ‹‹Progressing GIS›› በሚል መሪ ቃል ኅዳር 9/2013 ዓ/ም በፓናል ውይይት አክብሯል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ በመክፈቻ ንግግራቸው ባለንበት 21ኛው ክ/ዘመን የጂኦ ስፓሻል መረጃዎችና ቴክኖሎጂ ከመሠረተ ልማት፣ ከኮሚዩኒኬሽን፣ ከኃይልና ከሃይድሮሎጂ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመቅረፍ ያላቸው ፋይዳ ጉልህ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ በዚህ ረገድም ዩኒቨርሲቲው የጂ አይ ኤስና ጂኦ ኢንፎርማቲክስ ቤተ-ሙከራ በማስገንባትና ከተለያዩ በዘርፉ ከሚሠሩ ተቋማት ጋር በመተባበር በዘርፉ የሥልጠና፣ የመረጃና የምርምር ማዕከል ለመሆን እየሠራ ነው ብለዋል፡፡ የጂኦ ስፓሻል ሥርዓት በዩኒቨርሲቲያችን መዘርጋቱ ዩኒቨርሲቲው የምርምር ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ለሚያደርገው ጉዞ ፋይዳው ጉልህ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፉን የጂ አይ ኤስ (GIS) ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ አከበረ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አጋርነቱን አረጋገጠ

Tuesday, 17 November 2020 16:41

ማክሰኞ ኅዳር 08/2013 ዓ/ም ከቀኑ 5:30 ጀምሮ “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል በአገር ደረጃ እንዲካሄድ ለቀረበው አገራዊ ጥሪ መላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በየካምፓሱና በያለበት በመቆም ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያለውን አጋርነት በተግባር አረጋግጧል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በሁሉም የሀገራችን ዳር ድንበሮች በግምባር ቀደም ተሰላፊነት ለሀገራችን ሉዓላዊነትና ለሕዝባችን ክብር የሚከፍለውን መሥዋዕትነት በመዘከርና በማድነቅ ለ1 ደቂቃ ቀኝ እጅን በደረት ላይ በማድረግ እንዲሁም ለ 1 ደቂቃ ደግሞ ያለማቋረጥ በማጨብጨብ ለሠራዊቱ ክብር የመቆም ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አጋርነቱን አረጋገጠ

 

በዲታ ወረዳ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከልና የሸክላ ሠሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ያለመ ፕሮጀክት ተጀመረ

Thursday, 12 November 2020 17:27

2ኛ ዙር የደምባ ተፋሰስ አፈር መሸርሸር ቅነሳና የሸክላ ሠሪዎችን ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ማሻሻል ላይ ያተኮረ የምርምር ፕሮጀክት አጀማመር ውይይት በጋሞ ዞን ዲታ ወረዳ ጥቅምት 21/2013 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ስምዖን ሽብሩ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ 2011 ዓ/ም ላይ የተጀመረ ሲሆን ለሦስት ዓመታት የሚዘልቅ ነው፡፡ በመጀመሪያው ዓመት መረጃዎችን የመሰብሰብና መሬት ላይ ያለውን እውነታ የመለየት ሥራ የተሠራ ሲሆን በሁለተኛው ዓመት የአፈር ጥበቃ ሥራው ሲሠራ ሸክላ ሠሪዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሁኔታ ተለይቷል፡፡ በ2013 በጀት ዓመት ሙሉ በመሉ ወደ ትግበራ የተገባ መሆኑን ዶ/ር ስምዖን ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በአካባቢው ያሉ አርሶ አደሮች መሬት በጎርፍ እንዳይጎዳ ከማድረጉ ባሻገር የዲታ ወረዳ ከፍተኛ ቦታዎች የዓባያና ጫሞ ሐይቆች ገባር ወንዞች መነሻ ቦታ ስለሆኑ በገባር ወንዞች አማካኝነት ወደ ሐይቆቹ የሚገባው ደለልም ይቀንሳል ብለዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Read more: በዲታ ወረዳ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከልና የሸክላ ሠሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ያለመ ፕሮጀክት ተጀመረ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በዩኒቨርሲቲው ኬሚስትሪ ቤተ-ሙከራ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ የንጽህና መጠበቂያዎች አመራረት ሂደትን ጎበኙ

Tuesday, 10 November 2020 17:53

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በዩኒቨርሲቲው ኬሚስትሪ ቤተ-ሙከራ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ የንጽህና መጠበቂያዎች አመራረት ሂደትን አስመልክቶ ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም ጉብኝት አካሂደዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማኅ/አገ/ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ስምዖን ሽብሩ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው የምርምርና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶችን ወደ ማኅበረሰቡ በማሸጋገር የሥራ ዕድል ለመፍጠርና የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማጎልበት እየሠራ ነው፡፡ ከዚህም አንፃር ኮቪድ-19 ከተከሰተ ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ 39 የምርምርና የፈጠራ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ ከምርምርና የፈጠራ ሥራዎቹ መካከልም በኬሚስትሪ ቤተ-ሙከራ እየተዘጋጀ የሚገኘው የንጽህና መጠበቂያዎችን የማምረት ሂደት ይገኝበታል ብለዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በዩኒቨርሲቲው ኬሚስትሪ ቤተ-ሙከራ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ የንጽህና መጠበቂያዎች አመራረት ሂደትን ጎበኙ

 

Page 6 of 269

«StartPrev12345678910NextEnd»