የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ጋር በመተባበር ‹‹ጠንካራ እና ታማኝ ሐኪም ለተሻለ ጤና!›› በሚል መሪ ቃል በኮሌጁ ሥር ለሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች ታኅሣሥ 17/2013 ዓ/ም በሙያ ማሻሻያ ዙሪያ ሥልጠና የሰጠ ሲሆን የጋራ መግባቢያ ሰነድም ተፈራርሟል፡፡   ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንትነት እና ለምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንትነት ኅዳር 21/2013 ዓ/ም ባወጣው ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ መሠረት የውድድሩ አካል የሆነው ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ገለጻ ታኅሣሥ 7/2013 ዓ/ም ለሴኔቱ ቀርቧል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቤኔፊት ሪያላይዝ (BENEFIT REALISE) ፕሮግራም ከደራሼ፣ ምዕራብ ዓባያ፣ ቁጫ እና ዛላ ወረዳዎች 16 ቀበሌያት ለተወጣጡ የግብርና ባለሙያዎች ከታኅሣሥ 1-2/2013 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የተዘጋጀውና የእንሰት እርሾን ለረዥም ጊዜ በቤተ-ሙከራ ለማስቀመጥና ለአርሶ አደሮች አባዝቶ ለማከፋፈል ያለመው ፕሮጀክት ከዓለም ዓቀፉ የዘረመል ምኅንድስና እና ባዮቴክኖሎጂ ማዕከል የ45 ሺህ ዩሮ ድጋፍ አግኝቷል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ትምህርት ቤት ከተማሪዎች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ላላቸው የሥነ-ልቦና፣ ጋይዳንስና ካውንስሊግ እና የዜሮ ፕላን ባለሙያዎች፣ የተማሪዎች አገልግሎት ሠራተኞች እንዲሁም የተማሪዎች መኝታ ቤት፣ የምግብ  አገልግሎት፣ የሰላም ፎረምና የደኅንነትና ጥበቃ አስተባባሪዎች የአዕምሮ ጤና፣ ሥነ ልቦናና ማኅበራዊ   አገልግሎት አሰጣጥንን በተመለከተ ከኅዳር 10-11/2013 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ