- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተቋማዊ ለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በውስጣዊና ውጫዊ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ኅዳር 11 /2013 ዓ/ም ውይይት አካሂዷል፡፡
Read more: በዩኒቨርሰቲው ውስጣዊና ውጫዊ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ውይይት ተካሄደ
- Details
በኮንሶ ዞንና አካባቢው በተከሰተው የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለሚገኙ ወገኖች ዩኒቨርሲቲው ልዩ ልዩ ኅዳር 15/2013 ዓ/ም ድጋፍ አድርጓል፡፡ በዕለቱ 156 ፍራሽ፣ 28 ካርቶን ሳሙና እና 5 እሽግ የሴቶች የንጽህና መጠበቂያዎች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ከተፈናቃዮቹ በቀረበው ጥያቄ መሠረትም የውሃ አቅርቦት እና የጤና አገልግሎት እየተሰጣቸው ነው፡፡
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከኮንሶ ዞን ጉማይዴ አካባቢ በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ
- Details
የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ሕግ በማስከበር ሂደት ላይ ጉዳት ለደረሰባቸውና ደም ለሚያስፈልጋቸው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት አጋርነታቸውን ለመግለጽ ኅዳር 14/2013 ዓ.ም በሁሉም ካምፓሶች ደም የመለገስ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ትምህርት ቤት ከተማሪዎች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ላላቸው የሥነ-ልቦና፣ ጋይዳንስና ካውንስሊግ እና የዜሮ ፕላን ባለሙያዎች፣ የተማሪዎች አገልግሎት ሠራተኞች እንዲሁም የተማሪዎች መኝታ ቤት፣ የምግብ አገልግሎት፣ የሰላም ፎረምና የደኅንነትና ጥበቃ አስተባባሪዎች የአዕምሮ ጤና፣ ሥነ ልቦናና ማኅበራዊ አገልግሎት አሰጣጥንን በተመለከተ ከኅዳር 10-11/2013 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ትምህርት ቤት የአዕምሮ ጤና፣ ሥነ-ልቦናና ማኅበራዊ አገልግሎትን በተመለከተ ሥልጠና ሰጠ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን ማኅበር፣ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት በመተባበር ለውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የውሃ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም በሚያስችሉ አዳዲስ ሶፍትዌሮች ዙሪያ ከጥቅምት 30 - ኅዳር 04/2013 ዓ/ም የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ለውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የሶፍትዌሮች ሥልጠና ተሰጠ