የዩኒቨርሲቲው ሕግ ት/ቤት ከእንግሊዙ ኦክስፎርድ ብሩክስ /Oxford Brookes/ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመማር ማስተማር፣ በምርምርና በመምህራን ልማት ላይ በጋራ እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡ በዚህም መሠረት ከኦክስፎረድ ብሩክስ ዩኒቨርሲቲ የመጡ ተማሪዎችና ፕሮፌሰሮች ከዩኒቨርሲቲው ሕግ ት/ቤት ተማሪዎች ጋር የጋራ የመስክ ትምህርት እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ ምስሉን ለማየት ከዚህ ይጫኑ

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁለተኛ መንፈቀ-ዓመት በመደበኛና በማታ እንዲሁም በሣምንት መጨረሻ መርሐ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡

icon ለበለጠ መረጃ ይህንን ይጫኑ

ከታኅሣሥ 14/2012 ዓ/ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የተማሪዎች ኅብረት የፓርላማ አባላትና አመራሮች ምርጫ ጥር 03/2012 ዓ/ም የኅብረቱ የሥራ አስፈጻሚ እንዲሁም የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ አባላትን በመምረጥ ተጠናቋል፡፡

በዚህ መሠረት ተማሪ አንዳርጋቸው ደስታ የኅብረቱ ፕሬዝደንት፣ ተማሪ የትምወርቅ ክብሩ ም/ፕሬዝደንት እንዲሁም ተማሪ ቃልኪዳን አባይነህ ዋና ፀሐፊ በመሆን ተመርጠዋል፡፡ በተጨማሪም ተማሪ ገነት ካሳዬ፣ ተማሪ ሀለፎም ደረጀ እና ተማሪ ሚልኪያስ ሙርቴ የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ አባላት ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ምስሉን ለማየት ከዚህ ይጫኑ

የዩኒቨርሲቲው የሕክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ የማስተማሪያና ሪፌራል ሆስፒታሉን ጨምሮ ቀደም ሲል ከነበረው አደረጃጀት ከፍ ባለ ደረጃ እንዲደራጅ ተጠንቶ ተወስኗል፡፡ በዚህ መሠረት ኮሌጁ በ‹ቺፍ ኤክስክዩቲቭ ዳይሬክተር› እንዲመራ የዩኒቨርቲው የሥራ አመራር ቦርድ ታኅሣሥ 10/2012 ዓ/ም ባካሄደው ስብሰባ ወስኗል፡፡ ምስሉን ለማየት ከዚህ ይጫኑ

እ.አ.አ ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ ለ4 ዓመታት ሲካሄድ የቆየው የVLIR እንሰት ፕሮጀክት የማጠቃለያ ወርክሾፕ ጥር 12/2012 ዓ/ም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ በፕሮጀክቱ አማካይነት በጋሞ ደጋማ አካባቢዎች በእንሰት አመራረት ሂደትና በእንሰት አጠውላጊ በሽታ ዙሪያ የተደረጉ የምርምር ሥራዎች ቀርበዋል፡፡ በዕለቱ ዩኒቨርሲቲው ከኢትዮጵያ ባዮ-ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባባር የእንሰት ምርት አዘገጃጀትና ድኅረ-ምርት አያያዝን በቴክኖሎጂ ፈጠራዎች የሚያግዝ አዲስ ፕሮጀክትም ይፋ አድርጓል፡፡ምስሉን ለማየት ከዚህ ይጫኑ