የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከIBRO እና DANA ፋውንዴሽኖች ጋር በመተባበር የአንጎል ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንትን ምክንያት በማድረግ ለኮሌጁ መምህራን፣ ተመራማሪዎችና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች እንዲሁም ለመሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከታኅሣሥ 12-16/2013 ዓ.ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ የአዕምሮ ጤና ምንነት፣ የአዕምሮ ጤና እድገት እና የአዕምሮ ጤናን የሚጎዱ ሱሶችና አደንዛዥ ዕጾች የሥልጠናው ይዘቶች ናቸው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የጤና ሚኒስቴር ልዑካን ቡድን ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና ከጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ባለድርሻ አካላት ጋር የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ አፈፃፀምን ታኅሣሥ 16/2013 ዓ/ም ጎብኝቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ጋር በመተባበር ‹‹ጠንካራ እና ታማኝ ሐኪም ለተሻለ ጤና!›› በሚል መሪ ቃል በኮሌጁ ሥር ለሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች ታኅሣሥ 17/2013 ዓ/ም በሙያ ማሻሻያ ዙሪያ ሥልጠና የሰጠ ሲሆን የጋራ መግባቢያ ሰነድም ተፈራርሟል፡፡   ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንትነት እና ለምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንትነት ኅዳር 21/2013 ዓ/ም ባወጣው ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ መሠረት የውድድሩ አካል የሆነው ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ገለጻ ታኅሣሥ 7/2013 ዓ/ም ለሴኔቱ ቀርቧል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቤኔፊት ሪያላይዝ (BENEFIT REALISE) ፕሮግራም ከደራሼ፣ ምዕራብ ዓባያ፣ ቁጫ እና ዛላ ወረዳዎች 16 ቀበሌያት ለተወጣጡ የግብርና ባለሙያዎች ከታኅሣሥ 1-2/2013 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡