በ2012 ዓ/ም ሊሰጥ የነበረው ሀገር አቀፍ የሕግ መውጫ ፈተና (Exit Exam) በኮቪድ-19 መከሰት ምክንያት ወደ 2013 ዓ/ም መተላለፉ ይታወሳል፡፡

ስለሆነም ፈተናው የሚሰጠው ከኅዳር 1-4/2013 ዓ/ም በመሆኑ ፈተናውን መውሰድ የምትፈልጉ በሙሉ ከጥቅምት 2-12/2013 ዓ/ም ድረስ ብቻ ብር 664.00 ( ስድስት መቶ ስልሳ አራት ብር ብቻ) በኤጀንሲው የባንክ ሒሳብ ቁጥር 0171597578400 ገቢ ያደረገባችሁበትን ደረሰኝ በመያዝ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ት/ቤት ቀርባችሁ መመዝገብ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡

ለድህረ ምረቃ አዲስ አመልካቾች በሙሉ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድህረ ምረቃ ት/ቤት ለ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን እየመዘገባ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

መስከረም 30 ዕለተ ቅዳሜ 2013 ዓ/ም ሊሰጥ የነበረው የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና ፈተናው የሥራ ቀናት ላይ እንዲሆን ከተለያዩ አመልካቾች ጥያቄ በቀረበው መሠረትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ምክንያት ፈተናው ለ3ኛ ጊዜ ለጥቅምት 09 ዕለተ ሰኞ 2013 ዓ/ም የተዛወረ መሆኑን ከይቅርታ ጋር እንገልፃለን፡፡

የዩኒቨርሲቲው ካውንስል መስከረም 20/2013 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው የ2013 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ ላይ ውይይት በማድረግ አፅድቋል፡፡ ለዕቅዱ ማስፈጸሚያ ለመደበኛ እና ለካፒታል በድምሩ ብር 1,594,367,000 ተመድቧል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ለድህረ ምረቃ አዲስ አመልካቾች በሙሉ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድህረ ምረቃ ት/ቤት ለ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን እየመዘገባ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ትናንት በወጣው የፈተና ጊዜ ማስታወቂያ በ25/01/13 ዓ/ም ሊሰጥ የነበረው የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና በአመልካቾች ጥያቄ መሠረት ለ30/01/13 ዓ/ም የተዛወረ መሆኑን እየገለፅን ተፈታኞች በተጠቀሰው ቀን ከጥዋቱ 02፡30 ጀምሮ በየተመደባችሁበት የመፈተኛ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡