የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ፈጠራ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል ከዚህ በፊት ሲሠራ እንደቆየው ሁሉ በተማሪዎች መካከል የቢዝነስ ሃሳብ (Business Idea) ውድድር በማካሄድ አሸናፊዎችን መሸለም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የቢዝነስ ሃሳብ (Business Idea) በማዘጋጀት መወዳደር የምትፈልጉ ተማሪዎች በውድድሩ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡ ከምዝገባ በኋላ ስለቢዝነስ ዕቅድ አዘገጃጀት ሥልጠና የምንሰጥ መሆኑን እየገለጽን፡-

•    የመመዝገቢያ ጊዜ - ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 17/06/2015 ዓ/ም ድረስ
•    የመመዝገቢያ ኢሜይል አድራሻ - This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ሲሆን ስም፣ ስልክ፣ ትምህርት ክፍላችሁን፣ ስንተኛ ዓመት እንደሆናችሁ እና የምትወዳደሩበትን የቢዝነስ ሃሳብ አጭር መግለጫ (ከ1 ገፅ ያልበለጠ) ከላይ ባለው የኢሜይል አድራሻችሁን እንድትልኩልን እናሳውቃለን፡፡
                                                                                                                                                                                                                                የአ/ም/ዩ የሥራ ፈጠራ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል