አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የእስልምና እና የክርስትና ሃይማኖቶች ተከታይ ለሆነው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብና የቀድሞ ምሩቃን እንዲሁም ለመላው የእምነቶቹ ተከታዮች እንኳን ለነብዩ መሐመድ 1,498 የልደት በዓል እና ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ እያለ በዓላቱ የሠላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆኑላችሁ ከወዲሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሳውላና ጂንካ ከተሞች በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብር በኅብረሰተሰብ ጤና ትምህርት የ2ኛ ዲግሪያቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች የልማታዊ የቡድን ሥልጠና ፕሮግራምን/Developmental Team Training Program /DTTP/ መሠረት በማድረግ በሳውላ ዶዛ ቀበሌ የላ ቀጠና እንዲሁም በጂንካ ብሩህ ተስፋ ንዑስ ቀበሌ በኮይዳ ቀጥር ሁለት መንደር የአካባቢውን ማኅበረሰብ በማስተባበር ከሰባት መቶ ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነቧቸው የጋራ መጸዳጃና ሻወር ቤት እና የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች መስከረም 13 እና 14/2016 ዓ/ም በይፈ ተመርቀው ለማኅበረሰቡ ተላልፈዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሁሉ አቀፍ ሴክተር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት እና ከጋሞ ልማት ማኅበር ጋር በመተባበር ከከተማው ወጣት አደረጃጀት ለተወጣጡ ወጣቶች በሕይወትና የአእምሮ ውቅር    ዙሪያ ከመስከረም 8-11/2016 ዓ/ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ በቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ያሠለጠናቸውን 91 ወንድና 58 ሴት በድምሩ 149 የ6 ባች ተማሪዎች ለ2 ዙር  መስከረም 13/2016 ዓ/ም አስመርቋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ባች 1ኛ ዓመት ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች፣ የ2014 ባች 2ኛ ዓመት ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች እና የ2012 ባች 4ኛ ዓመት የህግ ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ቅበላ፣ ምዝገባ እና ትምህርት የሚጀመርበት ቀን እንደሚከተለው እንዲሆን ተወስኗል፡፡