
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከአዩዳ ኢን አክስዩን ከተሰኘ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት እና ከስፓኒሽ ዴቨሎፕመንት ኤጀንሲ ጋር በመሆን የሞሪንጋ ተክል ላይ በጋራ የሚሰራ የትብብር ፕሮጀክት ለማስጀመር በምዕራብ አባያ ወረዳ ዶሼ ቀበሌ እና በወላይታ ዞን አባላ አባያ በተሰኙ በተመረጡ ስፍራዎች የምሪንጋ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ዛሬ ነሐሴ 13/2017 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከአለም ዓቀፍ የደን ምርምር ማዕከል(CFOR) እና ከአግሮፎረስትሪ ጋር በመተባበር በደጋና ወይና ደጋ የአየር ጸባይ የሚለሙ ከውጭ ሃገር የመጡ ተባይና በሽታን መቋቋም የሚችሉ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የተለያየ የግራርና የባህር ዛፍ ዝርያ ያላቸው ችግኞችን በማባዛት ለምርምርና የዘር ምንጭ ለማድረግ በግርጫ የምርምር ማዕከልና በኦቾሎ ኦዶ ቀበሌ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ነሃሴ 14 2017 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ተባይና በሽታን መቋቋም የሚችሉና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የተለያዩ የግራርና የባህር ዛፍ ዝርያዎች ችግኝ ተከላ ተካሄደ

- Details
የደቡብ ኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ሐምሌ 19/2017 ዓ/ም በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድመት ለደረሰበት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ /ኦቶና / ሆስፒታል ነሐሴ 3/2017 ዓ/ም 6 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የደቡብ ኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ /ኦቶና/ ሆስፒታል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ