በዞናችን ጋጮ ባባ፣ ቦንኬ እና ካምባ ወረዳዎች የተከሰተውን የመሬት መንሸራተት አደጋን ተከትሎ በደረሰውን አስደንጋጭ እና መሪር ሐዘን ምክንያት በአርባ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ትምህርት ዘመን አጋማሽ ላይ የሚደረገው የተማሪዎች ምረቃ በዩኒቨርሲቲው ካላንደር መሠረት አለመካሄዱ ይታወቃል፡፡

 በዚህም ውድ ምሩቃን የሐዘኑ ተካፋይ በመሆን በትዕግሥት የምረቃ ቀናችሁን ስለጠበቃችሁ እናመሰግናለን፡፡ በተከሰተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ ሕይወታቸው ላላፉ እና ለተጎዱ ወገኖቻችን የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን ዳግም እየገለጽን ምረቃው ረቡዕ መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ/ም የሚካሄድ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ


ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት