አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም የ12 ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው የማካካሻ ትምህርት/Remedial Program/ ፕሮግራም ለመከታተል ያለፉትን ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በግል ከፍሎ ለመማር የሚፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

 1. የመመዝገቢያ መስፈርቶች

በ2014 ዓ.ም የ12 ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው የማካካሻ ትምህርት/Remedial/ ፕሮግራም ለመከታተል ያለፉ (እንደተፈተኑት የትምህርት ዓይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣  180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠውን ነጥብ የሚያሟሉ፡፡

 1. የሚያስፈልጉ የትምህርት መረጃዎች
  1. E.S.L.C.E/EHEEQC የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ ውጤት ካርድ ኦርጅናልና የማይመለስ ሁለት  ፎቶ ኮፒ
  2. ከ9 - 12 ክፍል ትራንስክሪፕት ኦርጅናልና የማይመለስ ሁለት ፎቶ ኮፒ
  3. የማይመለስ ሁለት ዶሴ (ክላሰር) እና ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ
  4. የማመልከቻ ክፍያ ብር 00 /ሀምሳ ብር/ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካንት ቁጥር 1000021480502 ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ ከማስረጃቸዉ ጋር ማያያዝ::
  5. የ8ክፍል ሚኒስትሪ ካርድ ኦርጅናልና የማይመለስ ሁለት ፎቶ ኮፒ
 2. የማመልካቻ ቦታ 

ሀ) አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነጭ ሣር ካምፓስ የተከታታይና ርቀት ትም/ት ኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

ለ)አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ የተከታታይ ትም/ት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት(የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብቻ)

 1. የምዝገባ ጊዜ - ከየካቲት 27/2015 - መጋቢት 07/2015 ዓ.ም ድረስ

ለተጨማሪ መረጃ - በ046-181-5468 እና 046-181-0228 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 ጥራት ያለው ትምህርት መለያችን ነው!!

 

 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ