ወ/ሮ እታገኝ ጓሉ ከአባታቸው ከአቶ ጓሉ ገብሬ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ወጋየሁ ጓሉ በቀድሞ ወሎ ክፍለ ሀገር በወልድያ ከተማ የካቲት 16/1974 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

ወ/ሮ እታገኝ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ ከተማ በኩልፎ መለስተኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ4 ዓመታት የቀለምና ንግድ ሥራ/Commerce/ ትምህርት ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡

ወ/ሮ እታገኝ ጓሉ የከፍተኛ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በ“Assistant Information Technology” የትምህርት መስክ በደረጃ II፣ በአልፋ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በርቀት ትምህርት በሴክሬተሪያል ሳይንስና ቢሮ አስተዳደር በደረጃ II እና በዙማ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ በ“Customor Contact and Secretarial Operations Coordination” ትምህርት መስክ በደረጃ IV  በማታው መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡

ወ/ሮ እታገኝ ጓሉ በአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከጥቅምት 5/1995 ዓ/ም - ሐምሌ 30/1996 ዓ/ም በቤተመጻሕፍትና መረጃ አገልግሎት በነጻ አገልግሎት፣ ከነሐሴ 3/1996 ዓ/ም - ሚያዝያ 30/2002 ዓ/ም በጊዜያዊ ኮንትራት በጸሐፊነት፣ ከግንቦት 1/2002 ዓ/ም - ኅዳር 30/2005 ዓ/ም በቢሮ ረዳትነት፣ ከታኅሣሥ 1/2005 ዓ/ም - ታኅሣሥ 30/2006 ዓ/ም በቋሚ ቅጥር በሴክሬተሪ I በጸሐፊነት፣ ከጥር 1/2006 ዓ/ም - ታኅሣሥ 30/2008 ዓ/ም በሴክሬተሪ II በጸሐፊነት፣ ከጥር 1/2008 ዓ/ም - ነሐሴ 30/2010 ዓ/ም በቤተመጻሕፍትና መረጃ አገልግሎት የኤሌትሮኒክስ ሪሶርስ አገልግሎት ባለሙያ በመሆን እንዲሁም ከመስከረም 1/2011 ዓ/ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኤክስኪዩቲቭ ሴክሬተሪ III በፀሐፊነት አገልግለዋል፡፡

ወ/ሮ እታገኝ ባለትዳር ሲሆኑ በወሊድ ላይ ባጋጠማቸው ችግር የካቲት 29/2015 ዓ/ም በ41 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በወ/ሮ እታገኝ ጓሉ ድንገተኛ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡

                                                                                                                 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

                                                                                                                  የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

                                                                                                              የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት