ወ/ሪት ፀሐይ በጆ በርሶ ከአባታቸው ከአቶ በጆ በርሶ እና ከእናታቸው ወ/ሮ አየለች ወ/ሥላሴ በጋሞ አውራጃ አርባ ምንጭ ከተማ ጥር 21/1970 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

ወ/ሪት ፀሐይ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ ከተማ ኃይሌ ደጋጋ 1ኛና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቀዋል፡፡

ወ/ሪት ፀሐይ በጆ የከፍተኛ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ ኦሞ መምህራን ተቋም በኮምፒውተር ሳይንስ  የትምህርት መስክ በዲፕሎማ፣ በሀርሞኒ የመኪና ጽሕፈት ት/ቤት /Harmony Typing School/ በመኪና ጽሕፈት ትምህርት በዲፕሎማ፣ በፓራሜድ ኮሌጅ በሂዩማን ሪሶርስ ሱፐርቪዥን /Human Resource Supervision/ ትምህርት መስክ በደረጃ  IV በማታው መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡

ወ/ሪት ፀሐይ በአርባ ምንጭ ኦሞ ትምህርት ኮሌጅ ከነሐሴ 12/1996 - ሰኔ 23/2000 ዓ/ም በፅዳትና ኅትመት ሥራ፣ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከታኅሣሥ 1/2004 ዓ/ም - ኅዳር 30/2005 ዓ/ም በጸጥታና ደኅንነት ክፍል በኮንትራት ቅጥር ለ1 ዓመት በፖሊስነት፣ ከታኅሣሥ 1/2005 ዓ/ም - ግንቦት 30/2005 ዓ/ም በሙከራ ቅጥር በጽሂ 6 ደረጃ፣ ከሰኔ 1/2005 ዓ/ም - ሐምሌ 30/2010 ዓ/ም በተማሪዎች አገልግሎት የተማሪዎች መኝታ ተቆጣጣሪ በጽሂ 7 እንዲሁም ከመስከረም 1/2011 ዓ/ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በዩኒቨርሲቲው ጫሞ ካምፓስ በቤተ-መጻሕፍት የፎቶ ኮፒና ጥረዛ ሠራተኛ በመሆን አገልግለዋል፡፡

ወ/ሪት ፀሐይ ባደረባቸው ሕመም የካቲት 30/2015 ዓ/ም በ45 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡   

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በወ/ሪት ፀሐይ በጆ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡

      አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ    
      የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
   የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት