አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በዓይነቱ ልዩ የሆነ ነጻ የዓይን ምርመራና የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና (Cataract Surgery) አገልግሎት ከአሜሪካ በሚመጡ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው የዓይን ስፔሻሊስት ሐኪሞች ጋር በመተባበር ከመጋቢት 25 - 30/2015 ዓ/ም ድረስ በሆስፒታሉ ይሰጣል፡፡

ስለሆነም በዓይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት የማየት ችግር ያለባችሁ ሕሙማን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የዓይን ሕክምና ክፍል ከመጋቢት 11 - 30/2015 ዓ/ም ድረስ በመምጣት የዓይን ምርመራ በማድረግ የቀጠሮ ወረቀት እንድትወስዱና የነጻ ሕክምናው አገልግሎት ተጠቃሚ እንድትሆኑ እያሳወቀ በማኅበረሰቡ ውስጥ በዓይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት ማየት ለተሰናቸው ወገኖች ሁሉም የማኅበረሰቡ አባል መረጃውን በማድረስ ትብብር እንዲያደርግ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ዓይነስውርነትን በጋራ እንከላከል!

ማሳሳቢያ

ለዓይን ሕክምና ቅድመ ምርመራ የምትመጡ ሕሙማን ካርድ ማውጣት የማይጠበቅባችሁ ስለሆነ በቀጥታ ወደ ዓይን ሕክምና ክፍል እንድትመጡ ይገልጻል፡፡

የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል

 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት