በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮሎጂ ት/ክፍል በ"Biodiversity Conservation and Management" ትምህርት ፕሮግራም የ3 ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ማቲዎስ አጊዜ የምርምር ሥራውን ነሐሴ 29/2015 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርቧል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ዕጩ ዶ/ር ማቲዎስ የመመረቂያ ጽሑፉን ያዘጋጀው ‹‹Vascular Plant Species Diversity, Ethnobotany, Phytochemical Analysis and Antibacterial Testing of Traditional Medicinal Plants in Dawuro Zone of Southwestern Ethiopia›› በሚል ርዕስ ላይ ነው፡፡

ዕጩ ዶ/ር ማቲዎስ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በተወለደበት ዳውሮ ዞን በማጠናቀቅ ዲፕሎውን በባዮሎጂ ትምህርት ከኮቴቤ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ በ1982 ዓ/ም፣ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ"ባዮሎጂ” በ1995 ዓ/ም እና ሁለተኛ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹Dry Land Biodiversity›› በ2000 ዓ/ም አግኝቷል፡፡ የ3 ዲግሪ ትምህርቱን ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ‹‹Biodiversity Conservation and Management›› ትምህርት ፕሮግራም ሲከታተል ቆይቷል፡፡

በግምገማ መርሃ ግብሩ የውስጥና የውጪ ገምጋሚዎችን ጨምሮ የኮሌጅ ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ የዘርፉ መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ታድመዋል፡፡

ዕጩ ዶ/ር  ማቲዎስ አጊዜ የዶክትሬት ዲግሪውን በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ከጸደቀ በኋላ የሚያገኝ ይሆናል፡፡

 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት